አብይ አህመድ በጂቡቲ የተደረገው የኢጋድ ስብሰባ ረግጦ መውጣቱን ኢትዮ ፎረም አረጋግጧል::
አብይ አህመድ በስብስባው ላይ ሲናገር “ሱዳናውያን የኬንያው መሪ ዊልያም ሩቶ ድርድሩን እንዲመሩ ፍላጎት የላቸውም ሱዳኖች ሩቶ ገለልተኛ ነው ብለው አያምኑም…” በማለት እኔ ድርድሩን ብመራው ይሻላል የሚል ሀሳብ የሰጠ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶም የአብይ ችግር very personal ነው ሲሉ ተናግረዋል::
አብይ አህመድ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በምስራቅ አፍሪካ ሪጅናል ቀጠና ላይ ከፍተኛ ተሰሚነት ማግኝታቸውና በምዕራባውያን ዘንድ ከሱ የበለጠ ተሰሚነትና ተፅእኖ ፈጣሪ መሆናቸው አብይ አህመድን እንዳበሳጨው ብዙ ጊዜ የተስተዋለ ሁኔታ ነው::
የኢጋድ አባል ሀገራት ስብስባውን የሚመሩት የጂቢቲ ፕሬዝዳንትም ከዊልያም ሩቶ ሀሳብ ጋር በመቆማቸውና ዊልያም ሩቶን በመደገፋቸው አብይ አህመድ ስብሰባውን ረግጦ ሊወጣ ችሏል:: የአብይ አህመድ ስብስባውን ረግጦ መውጣት ለድርድሩ ስኬት መልካም መንገድ መክፈቱን አባል ሀገራት የገለፁ ሲሆን አብይ አህመድ ስብስባውን ረግጦ ከወጣ በኃላ ሁለቱም የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል መልካም መንፈስ መፈጠሩን ምንጮች ያስረዳሉ::
ሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎችም አብይ አህመድ ከስብሰባው ከወጣ በኃላ መስማማታቸው አብይ አህመድ በድርድሩ ጣልቃ መግባት ውይይቱን ለረጅም ጊዜ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል:: አብይ አህመድ “እኔ የሰላም ሎሬት ተሸላሚ ሆኜ ሳለ ለምን ድርድሩም አልመራሁትም” በማለት በሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች መካከል ሲደረግ የነበረውን ስምምነት አብይ አህመድ ሲያውክ መቆየቱ ታውቋል::
ምንጭ: ኢትዮ ፎረም