December 13, 2023 

ዜናከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነታቸው ተነስተው አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነታቸው ተነስተው አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስተር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የንግድ ሥርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ተሻለ በልሁን ከኃላፊነታቸው አንስተው፣ በምትካቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ፍሰሃ ይታገሱን ሾመዋል።በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ሥርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ሆነው የተሾሙት አቶ ፍሰሃ ትናንት ታኅሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የሥራ ርክክብ በማድረግ ሥራ ጀምረዋል፡፡አቶ ተሻለ በልሁ ሚኒስትር ደኤታ ሆነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ዋና ዳይሬክተር እንደነበሩ የታወቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በዚሁ ሳምንት ውስጥ ከኃላፊነታቸው ያነሷቸው ሌላው ባለሥልጣን፣ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ናቸው። ባለፈው ሳምንት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታዎችን፣ ማለትም አቶ ዓለም አንት አግደውንና አቶ ፈቃዱ ፀጋን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በመሾም፣ አቶ ተስፋዬ ዳባን በፍትሕ ሚኒሰቴር የዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አድርገው ሾመዋል፡፡