ከአዲስ አበባ በሞጣ በኩል ወደ ባሕርዳር በሚወስደው መንገድ አዴት አካባቢ የሚገኘው ድልድይ መሰበሩን ዋዜማ ተረድታለች።
ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ድልድዩ ከተሰበረ ከሳምንት በላይ እንዳስቆጠረና የሰበረው አካል ማን እንደኾነ ግን በትክክል እንደማያውቁ ገልጠዋል።
በድልድዩ መሰበር ሳቢያ ወደ ባሕርዳር የሚጓዙ መንገደኞች ወንዙን በእግራቸው ተሻግረው፣ በሌሎች ተሽከርካሪዎች ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ ከደብረ ማርቆስ ወደ ባሕርዳር የትራንስፖርት አገልግሎት እስካሁን እንደተቋረጠ መኾኑን ዋዜማ ተገንዝባለች።
በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ፣ ባብዛኛዎቹ የጎጃም በወረዳዎች መካከል እንዲኹም በዞን ከተሞችና በባሕርዳር መካከል የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ለሳምንታት እንደተቋረጡ ናቸው።