December 13, 2023 – Konjit Sitotaw
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ትላንት ጧት የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት 13 ሰዎች መገደላቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምቻለኹ በማለት ዶይቸቨለ ዘግቧል፡፡
በሰዎቹ ላይ ጥቃቱ የደረሰው፣ ጆጅ ከተባለ ገጠራማ ቀበሌ ወደ ቡሬ ወረዳ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀሱ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል፡፡
ጥቃቱ የደረሰበት የጆጅ ቀበሌ ሥራ አስኪያጅ ሲሳይ አበዋ፣ ጥቃቱን ያደረሱት “ጽንፈኛ” ሲሉ የጠሯቸው ኃይሎች መኾናቸውን መግለጣቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል፡፡
በኡሙሩ ወረዳ በግጭቶችና ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በሚሰነዝሯቸው ጥቃቶች ሳቢያ፣ ከ10 ያህል ቀበሌዎች 49 ሺህ የሚደርሱ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ዘገባው አመልክቷል።