December 13, 2023 – Getachew Shiferaw
የአዲሱ ኢህዴን ንቀት!

ይህ መግለጫ የተሰጠው ተጠንቶና ታስቦበት እንዳልሆነ ይዘቱ ይናገራል። ይህ መግለጫ የተሰጠው ለታዬ ደንድኣ እስር ማስቀየሻ ነው። የአማራ ህዝብ ለአንድ የኦሮሞ ብልፅግና ታሳሪ ማስቀየሻ ጥሪ ነው የሚደረግለት።
ጥሪ አደረግን የሚሉት ቀልድ ነው። መሳሪያ ማስረከብ ነው። አርሶ አደሩንም በዛው መሳሪያ ለመቀማት። ሰላም አይፈልጉም ተብለው ሲጋለጡ “ሰላም ፈላጊ” መስለው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚሰሩት በአማራ ህዝብ ላይ ነው። የሰላም ጥሪ ብለው አብይ አህመድ ያዘዛቸውን ንቀት አስተላልፈዋል። አማራ ክልል ችግር እንዳይፈታ ተንኳሽ መግለጫ እንጅ የሰላም ጥሪ አይደለም። ከባሕርዳር ወደ ቅርብ ከተማ በመኪና መሄድ የማይችለው የአማራ ክልል አዲሱ አመራር /የአብይ አህመድ ኢህዴን/ “ትጥቅ ፍቱ” ብሎ መግለጫ ያወጣል።
ይህ በትዕዛዝ የተሰጠ መግለጫ የታዬን አጀንዳ ለመሸፈን ነው። የአማራ ክልል አመራር የአንድ ሰው እስር ዜናን ለመሸፈን ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ ንቀቱን ያቀረሻል።
አዲሱ የአማራ ክልል አመራር አማራ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን የሚንቅ አስመስሎ እንደነ ታምራት ላይኔ እየቀሰቀሰ ያለ፣ አማራው በድሮን ሲጨፈጨፍ የመከላከያ ደም ተመለሰ ብሎ የሚደሰት ጠላት ኃይል ነው። ይህ ኃይል በበረከት ስምኦን አማካሪነት፣ በሰማ ጥሩነህ መልማይነት አብይ አህመድ ያስቀመጠው አዲሱ ኢህዴን ነው!
አዲሱ ኢህዴን መሬት ላይ ያለውን ስለማይረዳ ትናንት እጅ ስጡ ብሎ መግለጫ ሰጥቶ ዛሬ የወሎ ዕዝ ፋኖ አደረጃጀት ተመስርቷል። አዲሱ ኢህዴን የአብይን ፍላጎት እንጅ መሬት ላይ ያለው ጉዳይ አያገባውም!
ይህ ኃይል እንደ ድሮው ኢህዴን አማራን ስሙን እያጠፋ፣ ክብሩን እያሳነሰ ማስገዛት ነው አላማው! ይህ ኃይል አማራን ለሌላ ዘመን ተሻጋሪ መሪ አልባነት፣ ለሌላ መዋቅራዊ በደል፣ ለሌላ መከራ ይዳርጋል!