
Wednesday, 13 December 2023 12:1
Written by Administrator


”አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል” -ድርጅቱ-አርቲስት ሀናን ታሪክ፤ ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ታዋቂና ግዙፍ የቻይና ኩባንያ ጋር የብራንድ አምባሳደር ለመሆን በዛሬው ዕለት በስካይላይት ሆቴል ከስምምነት ላይ የደረሰች ሲሆን፤ ለድርጅቱ የሁለት ዓመት የብራንድ አምባሳደር ለመሆን 10 ሚሊዮን ብር ተከፍሏታል፡፡ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ያቋቋመ ሲሆን ፤ ‹‹ኤስ›› በሚል ብራንድ ያልተለመዱና አዳዲስ የታሸጉ የኬክ ወይንም የጫፋጭ ምግቦችን እያመረተ በመላው አገሪቱ እያከፋፈለ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡ድርጅቱ ይህንን ‹‹ኤስ›› የተሰኘ ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማሳደግ የአንድ አመት የኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን እቅድ ማውጣቱን ገልጿል፡፡ በዚህ እቅዱ ውስጥም ታዋቂዋን አርቲስት ሀናን ታሪክን ማካተቱን አስረድቷል፡፡ ‹‹የኤስን ብራንድ ፕሮሞሽን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል›› ብሏል፤ ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ፡፡የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተ