የፋሽስቱ የኦሮሞ ብልጽግና ከፍተኛ የመንጋው አዛዦች ሲያደርጉት የሰነበቱትን ግምገማ አጠናቀቁ
መንጋው የኦሮሞ ብልጽግና ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድን ሲገማገም ሰንብቷል:: በስብሰባቸው በዋነኝነት በትኩረት የተወያዩባቸው አጀንዳዎች
1ኛ. ከኤርትራ ጋር በድብቅ የሚገናኙ ጀኔራሎችንና የኤርትራ እርዳታ ለአማራ ፋኖ ሰራዊትን በተመለከተ በአጽኖት ተወያይቷል:: ለኤርትራ በእኛ ውስጥ ሆነው መረጃ የሚያቀብሉ ጀኔራሎች አሉ: እኛ ማንነታቸውን ከማጋለጣችን በፊት እራሳቸው ግለ ሂስ ያንሱ ሲሉ የኦሮሞ ብልጽግና የአማራ ጀኔራል ተብየዎችን ሲያፋጥጧቸው መሰንበታቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባሊት መረጃ አዉጥተዋል።
በሌላ በኩል ኤርትራ እንደ አገር ፋኖን እየረዳች ነው ወይንስ አይደለም በሚል አጀንዳ ተወያይቶ ኤርትራ ፋኖን እንደ አገር እየረዳች አይደለም ነገር ግን የኤርትራ ጀኔራሎች በኮንትሮባንድ ለፋኖ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሳሪያና ተተኳሽ እያቀረቡ ነው: ፋኖን በእጅ አዙር እያስታጠቁ ነው ሲል ገምግሟል:: ይህንንም ለመከላከል በጥቁር ገበያ በኮንትሮባንድ የሚሸጠውን መሳሪያና ጥይት መንግስት በመግዛት ዋጋው ለፋኖ ውድ እንዲሆንበት ማድረግ አለብን በማለት የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጧል
2ኛ. የመስመራዊ መኮነኖችና ባለ ሌላ ማዕረግተኞች ከእኛ ጋር አይደሉም ሲል የፋሽስቱ ወራሪው የኦሮሞ ብልጽግና ጀኔራሎች (የጋማ_ከብቶች) ገምግመዋል:: የታችኛው የሰራዊት ክፍል ከእኛ ጋር ባለመሆኑ በአግባቡ እየተዋጋ አይደለም: ይከዳል: ሚስጥር ለፋኖ አሳልፎ እየሰጠ ነው በማለት ግምግሟል:: የመስመራዊ መኮነኖችን ከባድ ግምገማ በማድረግ ማጽዳት አለብን ሲል ወስኗል::
ህወሓት በ1993 ዓ.ም የድርጅቱን መሰንጠቅ ተከትሎ ሰራዊቱን ግምግሞ በማያስፈልጉት ላይ እርምጃ በመውሰዱ መንግስትን ታድጏል ሲል ወራሪው ገምግሟል:: እንዲሁንም ከሰራዊቱ ቢወጡም ለመንግስት አስጊ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን የአማራ ተወላጅ መስመራዊ መኮነኖችና የበታች ሹሞች ማሰር አለብን: አስፈላጊም ከሆነ ደግሞ መግ*ደል ካለብን እርምጃ መውሰድ አለብን ሲል ገምግሟል::
የመስመራዊ መኮነኖችና የበታች ሹሞች መንግስትን “ከራስ በላይ ለአገር” የሚለው የመከላከያ ሰራዊታችን እሴት ተቀይሯሮ ለድርጅቱ (ለብልጽግና) እንድንሰራ እየተደረግን ነው በማለት በየስብሰባው መንግስትንና ሰራዊቱን ለማራራቅ በጥያቄ ስም ሰራዊቱን እያነሳሱብን ነው ሲል ገምግሟል:: ይህንን አፍራሽ አካሄድ ለማክሸፍ ከምንወስዳቸው እርምቶች መካከል አንዱየተወሰኑ ክፍለ ጦሮችን መበወዝ ሰራዊቱ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን እርዕስ በርሱ እስከሚግባባ ድረስ ለመንግስት ስጋቱን ይቅንሳል ሲል ሃሳቡን ተወያይቶ ለስራው ተፈፃሚነት ለተስፈኛው አብርሃም በላይ የስራ ስምሪት ሰጥቷል::
3ኛ. ከትግራይና ከአማራ ጋር እያደረግነ ባለው ጦርነት የተሰው ወታደሮችን ቤተሰቦች የህይወት ካሳ ጠቀም ያለ ገንዘብ እንስጥ: በተለይ የአማራ ተወላጅ ሆነው ለተሰው የሰራዊት አባላትን ደጎስ ያለ ገንዘብ ለቤተሰቦቻቸው መስጠት አለብን ብሏል:: የአማራ ክልል ተወላጅ ሆነው በትግራይና አሁን በአማራ ክልል እያደረግነው ባለው ህግ የማስከበር ዘመቻ ለተሰው ወታደሮች ለእያንዳንዳቸው ከ180,000 ብር ጀምሮ እንደ ደረጃው ገንዘብ በመስጠት የሰራዊቱንና የቤተሰቦቻቸውን ድጋፍ ማግኘት አለብን ብሎ ተወያይቷል
4ኛ. የፋኖ ታጣቂ ኃይልን የሚገዳደር ኃይል በአማራ ክልል መፍጠር አለብን:: የተወሰኑ ከአማራ ክልል አድማ ብተናና ከመከላከያ ሰራዊቱን ለቀው የኮበለሉ በማስመሰል በእኛ ሰው እንዲመሩ በማድረግ የፋኖን ኃይል የሚገዳደርና የፋኖን አንድነት የሚያላላ ኃይል መፍጠር አለብን ሲል ተወያይቷል::
እንዲሁም በደቡብ ወሎና በኬሚሴ ግንባር ያሉትን ደጋፊዎቻችን በማሰልጠንና የተሻለ ትጥቅ በማስታጠቅ በአካባቢው ፋኖን እንዲዋጋ ማድረግ አለብን ብሏል:: ሰሞኑን ከኦሮሚያ ክልል ወደ አማራ ክልል ኬሚሴ ሄደው በቦታው ያለውን የጸጥታ ኃይል እያሰለጠኑ ነው: መከላከያ ሚኒስትር አስፈላጊውን ትጥቅ በአስቸኳይ እንዲያቀርብላቸው መመሪያ ተቀብሏል:: አማራውን ባለበት በማዳከም ትግሉ አስልች እንዲሆን በማድረግ የፋኖን ግስጋሴ ማቀጨጭ እንችላለን ሲል ወራሪው የኦሮሞ ብልጽግና ሃሳቡን ደምድሟል::
አሻራ ሚዲያ