December 15, 2023 – Konjit Sitotaw

በአዲስ አበባ አዳነች አቤቤ ከሚመሩት ከአዲስ አበባ መስተዳደር እና ከተለያዩ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮዎች ነባር ሰራተኞች የምዘና ፈተና በሚል ሴራ የኦሕዴድ ብልጽግና ከስራ አሰናብቶ በምትካቸው ካድሬዎቹን የመሰግሰግ እቅድ እንደያዘ ምንጮች ገለጹ። ይህ አዲስ አበባን ኦሮሙማ የማድረግ ሂደት አንዱ የእቅድ አካል የሆነው ሴራ በምዘና ፈተና ሰበብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የማባረር እቅድ ሲሆን አዳነች አቤኤ ይህን እቅድ ለማስፈጸም እንቅስቃሴ የጀመረች መሆኑ ሲሰማ በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ ያሉ በተለይ የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረው የኦሕዴድ ብልፅግና እቅድ በሚባረሩ ሰራተኞች ምትክ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎቹን ሰብስቦ ለመመደብ ዝግጅቱን አጠናቆ ለነባር ሰራተኞች የምዘና ፈተና ለመጀመር ተዘጋጅቷል።

አዳነች አቤቤ ይህ እቅድ ለማሳካት ከመስተዳደሩ ጀምሮ እስከ ወረዳ መዋቅር ድረስ የምዘና ፈተናው እንዲሰጥ እየሰራች ሲሆን በዚህ የምዘና ፈተና ሴራ በርካቶች ከስራቸው እንደሚፈናቀሉ ተረጋግጧል። ይህ የፖለቲካ ሴራ ያዘለው የምዘና ፈተና በአግባቡ እንደማይከናወን በርካቶች ይስማሙበታል። አንድ ዘገባ እንደጠቆመው አዲስ አበባ መስተዳድር በስሩ ለሚገኙ ከጽህፈት ቤት እስከ ወረዳ ደረጃ መዋቅር ላሉ ሰራተኞቹ የምዘና ፈተና  ከተሰተ በኃላ ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ በአቅማቸው ይመደባሉ አልያም መቋቋሚያ ተከፍሏቻው ከስራ ይሰናበታሉ። ከሰሞኑ ፈተናውን የሚወስዱ ተቋማት ተለይተዋል። ሁሉም ሰራተኞች እስከ ጥር ወር ድረስ ለፈተና ይቀመጣሉ። ከጥር በኋላ በርካታ ሺዎች ከስራቸው የተፈናቀሉ የመንግስት ሰራተኞች  አዲስ አበባ ትጥለቀለቃለች ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

በመጀመሪያው ዙር የብቃት ምዘና ፈተና የሚሰጠው ለቤቶች ልማት አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት፣ የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ፅሕፈት ቤት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅሕፈት ቤት፣ ኅብረት ሥራ ፅሕፈት ቤት እና የመሬት ልማት አስተዳደር ፅሕፈት ቤት ሲሆን፤ የብቃት ምዘናው በክፍለ ከተሞች እና በከተማው አስተዳደር ጭምር ባሉት መዋቅሮች እንደሆነ ከተያዘው እቅድ ለመረዳት ተችሏል። ከነዚህ ተቋማት የምዘና ፈተና ሴራ ተጠቂዎቹ መቋቋሚያ ተሰቷቸው ከስራ እንደሚሰናበቱ የወረደው መመሪያ ያሳያል። ይህንን የሚያስፈጽም ኮሚቴ በየክፍለከተማውና ወረዳው መቋቋሙም ተሰምቷል። ተፈትነው ማለፍ ለማይችሉ ሠራተኞች ከሥራ እንዲቀነሱ ምክንያት ይሆናል የሚል ብርቱ ስጋት በስፋት እየተስተዋለ ነው።

በምትኩ አዳዲስ ሰራተኞች እንደሚመጡና የብቃት ምዘና ፈተናውን ተከትሎ ከከተማ አስተዳደሩ ቢሮዎች እና የክፍለ ከተማ መመሪያዎች ይልቅ የወረዳ ጽህፈት ቤቶች የበለጠ የሰው ኃይል እንዲኖራቸው ሊደረግ እንደሚችልም ተመላክቷል። ዋዜማ የተባለው የዜና ምንጭ ያነጋገራቸው የቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በባለሙያነት የሚያገለግሉ ነባር ሠራተኛ እንዳሉት ደግሞ፣ እስከ ትናንት ሐሙስ ድረስ የክፍለ ከተማው አመራሮች ከሠራተኞቹ ጋር ምንም ዓይነት ውይይት አለማድረጉን ጠቅሰው፣ በዚኽ የተነሳም ሠራተኛው ልንባርረ እንችላለን በሚል ከባድ ስጋት ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል። “ከተለያዩ የትምሕርት መስኮች እንደመምጣታችን፣ በምን መልኩ ለፈተናው መዘጋጀት እንዳለብን እንኳን ባለማወቃችን ተጨንቀናል ሲሉ ተናግረዋል።