December 16, 2023 – Konjit Sitotaw
ታሪካዊቷ ግሸን ደብረ- ከርቤ በከባድ መሳሪያ እየተደበደበች ነው።በገዳዩ አብይ አህመድ ቅርስ እንዳወድም ትዕዛዝ የተሰጠው ጨፍጫፊ ኃይል የመስቀሉ መገኛ በሆነችው በዳግማዊት ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ቤተ-ክርስትያን ላይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ መፈጸሙን በስልክ ያነጋገራቸው የቤተ-ክርስትያኑቱ አባቶች እና ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የፋኖ ጦር ጋር ገጥሞ 6 መኪና ሙሉ ሰራዊቱ የአምባሰል ተራራ በልቶት የቀረው የአገዛዙ ኃይል በርቀት በሚተኮስ ከባድ መሳሪያ ምንም በሌለበት ቤተ- ክርስትያኗ ኢላማ ያደረገ ተኩስ እያደረገ ነው ብለዋል።
ትናንት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ አምባሰል ተለያየን እና ሮቢት በሚባል ቦታ በነበረው ውጊያ ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል። የቦታው አቀማመጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ለጎለህ ስላሴ በሚባል አካባቢ አንድ ፓትሮል የአገዛዙ ወታደር መኪና ገደል መግባቷን ተመልክተናል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዉልናል። ከዚህ በተጨማሪ ተለያየን አካባቢ ሶስት የአገዛዙ ወታደራዊ መኪኖች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
ከዚሁ ተለያየን ከተባለው ቦታ ወደ አምባሰል ተራራማ ስፍራዎች ከባድ መሳሪያ ሲተኮስ መዋሉን ገልፀዋል። ውጊያው የተቀሰቀሰው ገዳዩ ሰራዊት ወደ ደላንታ ለመምጣት እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነው ብለዋል። ዛሬ ከደላንታ አውጠንጥኝ ከሚባል አቅጣጫ ወደ ወገልጤና የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየተተኮሠ እንደሆነ እና አንድ የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ ወገልጤና ከተማው አቅራቢያ እንዳረፈ ተነግሯል።