ቲሊሊ ወረዳ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች!
በትናንትናው ዕለት ማለትም ታህሳስ 07/2016 ዓ.ም ከቲሊሊ ወረዳ ወጥቶ ወደ ሠከላ ወረዳ ለመግባት በመንገድ ላይ እያለ አሽፋ መገንጠያ ላይ በቲሊሊ ወረዳ ፋኖዎች መመታቱን ገልፀን ነበር። የመከላከያ 15(አስራ አምስት) የፊት አብሪዎችን በመምታት ድሉን የጀመረው የቲሊሊ ጀግና ፋኖ ሙሉው መከላከያ ከቲሊሊ ወጥቶ አሽፋ ላይ ፋኖን ቢገጥምም የፋኖን ጉልበት ስላልቻለ ወደየ አቅጣጫው በጫካ ተበትኖ ማደሩን አረጋግጠናል።
የወንበዴው ቡድን መከላከያ ተብየው በዛሬው ዕለት ማለትም ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም በሶስት ካሶኒ የጭነት መኪና በሸራ እየጠቀለለ ሬሳ መሠብሠቡ ታውቋል። የቲሊሊ አናብስቶችም መከላከያ ካንብ አድርጎት በነበረው የቲሊሊ ወረዳ የአትሌቲክስ መንደር (አሲንዳቦ ሜዳ) በመግባት የመከላከያ የትጥቅ ልብስ ጫማዎችን ጨምሮ የማህበረሰቡና የተለያዩ የእስረኞችን ከአንድ ኩንታል በላይ ስልክ እንዲሁም ጥይትና የተለያዩ ተተኳሾችን በመማረክ ወደ ግሉ አዙሯል። የቲሊሊ ወረዳ ከተማም በፋኖ ቁጥጥር ስር ሁናለች።
የሠከላ፣ የሳትሚያ ዳንጊያ፣ የአዲስ ቅዳም፣ የሁዲት፣ የሺንዲ፣ የቡሬና ሌሎች አቅራቢያ ፋኖዎች ለማገዝ እንደተንቀሳቀሱም ለማወቅ ተችሏል።
ሽንፈቱን ማመን ያቃተው የኦሮሙማው የብልፅግና ተላላኪ ቡድን ማህበረሰቡንና ህፃናትን በጭካኔ እየገደለ ሲሆን ከባድ መሳሪያም ወደ ሠብልና ወደ ገጠር ቤቶች እየጣለ እንደሆነ ታውቋል።
አሻራ ሚዲያ