December 18, 2023 – Konjit Sitotaw
የቻግኒ ሙስሊሞች የአምሳለ ኦነጉን መሪ አየር አሳጠሩት!
ይህ እንግዳ ዳኛው የአገዛዙ የአዊ ዞን አስተዳዳሪ ሌሎች 2 የኦሮሙማ ስምሪቶች አሉት። እነሱም 1) እንደ እናት ጡት 2 ሁነው የሚንከላወሱትን ሸንጎ (አምሳለ ኦነግ) ለሚባሉ ስብስቦች ስምሪት ሰጭነትና፣ 2) የአካባቢው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢነት ናቸው።
ታዲያ ሰሞኑን በቻግኒ ከተማ ህዝበ ሙስሊበ ሙስሊሙን ሰብስቦ “ፋኖ ዓላማ አሃዳዊ እምነት ለመገንባት ነው፣ አገሩን ኦርቶዶክስ ብቻ ለማድረግ ነው” እያለ ለታዳሚ መስበክ ይጀምራል።
በሳሎቹና የተማሩት የቻግኒ ሙስሊሞች እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረቡለት።
”ፋኖ አሀዳዊ ከሆነና ለኦርቶዶክስ እምነትን ለማስፋፋት ከሆነ እየታገለ ያለው “የአገው ብሔር ከ95% በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዬች ናችሁ እና ለምን የፋኖን ሀሳብ ትቃወማላችሁ?” ይሄኔ የመድረክ መሪው አይኑ ፍጥጥ ጥርሱ ግጥጥ አለ።
ወጣቶች እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ “ከእዚህ ቡኋላ ፋኖ የአንድ ሃይማኖት አቀንቃኝ፣ አሀዳዊ እምነት ገንቢ የሚል ከፋፋይ ሃሳብ በእኛ ዘንድ ቦታ የለውም፤ እኛ አማራዎች እኛ አገዎች ለዘመናት በሀይማኖት እኩልነት ተቻችለን እየኖርን ያለን አንድ ህዝብ ነን፤ ትናንተ በተፈጠረ የሸንጎ ፖለቲካ ልትሰሩብን አታሰቡ፤ አገው አማራ ነው አማራም አገው ነው” ብለው በብስጭት ማይኩን አስቀምጠው አዳራሹን ለቆ በመውጣታቸውን ወላሂ ብየ እምልልሀለው ያሉን የምንወዳቸውና የምናከብራቸው የአካባቢው ምንጮቻችን ገልፀዋል።