December 18, 2023 – Konjit Sitotaw
“እነ ብርሃኑ ጁላ በቶሎ እጃቸውን ይስጡ!” ደጉ ሻለቃ-
ለማጥቃት የሄደ ኃይል በዛው ቀረ።
“ብርሃኑ ጁላ የህጻን ልጅ ንግግር ነው የሚናገረው፣ አንድ ኤታ ማጆር ሹም ፈጽሞ የማይጠበቅ ነግግር ነው የሚናገረው፣ ከጫት ቤት መልስ በምርቃና የሚናገር ነው የሚመስለኝ፣ ብርሃኑ ጁላም ሆነ አረጋ ከበደ የሚናገሩት ሌላ መሬት ላይ ያለው እውነታ ሌላ። እኛ እጅ የምንሰጥበት ሳይሆን እነሱ እጅ የሚሰጡበትን ሁኔታ ነው ዛሬ መሬት ላይ እየሆነ ያለው”’ የፋኖ አመራር ለአንከር ሚዲያ ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ።
በመሬት ላይ ውጊያ ፋኖን መቋቋም ሲያቅተው፣ ንጹሃንን በድሮን መጨፍጨፍ፣ በከባድ መሳሪያ ከተሞችን ማውደም፣ ቤተ ክርስትያንና ት/ቤቶችን እንደ ምሽግ መጠቀም። እሁን ደግሞ አለሁ ትልቅ ነኝ ለማለት የአረቦችን አየር ሃይል አምጥቶ የአየር ላይ ትርእት ማሳየት “አልሞትኩም ብዩ አልዋሽም” ነው።
“ሸለፈታም” ማለት ቃል ኪዳን የሌለው ማለት ነው፣ ጀግናው አቶ ታየ ደንድአ አጥንቱ ድረስ እንደነገረው በጎልያድ የሚመሰለው ቃሉን የማይጠብቅ ብቻ ሳይሆን “በህዝብ ደም የሚጫወት አረመኔ” አብይ አህምድና ፣ የደነዘዙት ባለስልጣኖቹ ናቸው። ወደ ስልጣን ሲመጣ ስለ ዴሞክራሲ፣ ፍትህ፣ የህግ የበላይነት፣ እኩልነት፣ የገባውን ቃል በተደጋጋሚ ያጠፈና የረገጠ አጭበርባሪ ፣ ነውረኛ፣ ከሃዲ፣ አረመኔ ቃላቶች ተደምረው አብይ እህመድን አይገልጹትም። በዳዊት የሚመስለው ደግሞ በኦሮሚያ ብልጽግና/ብልግና ግፈኛ፣ ዘረኛ፣ ነውረኛና፣ ፋሽስታዊ ቡድን የተጨፈጨፈው፣ የተፈናቀለው፣ ይህ ነው ለማይባል፣ ባህላዊ፣ መዋቅራዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያው ጥቃት ለሚደርስበት ለአማራ ህዝብ ህልውና እንዲሁም ለመላ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፍትህን እኩልነት እውን ለማድረግ መስዋእትነት በመክፈል ላይ የሚገኘው ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ሃይሎች ናቸው።