December 19, 2023 

በባለጊዜዎች የሚፈጸመው ስርዐት አልበኝነትና ሕገወጥነት ለሕግ የበላይነት የማይጨነቀው የአብይ አገዛዝ አቅመቢስነትን በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ነው። የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የተሳነው አገዛዝ ካድሬዎቹ ራሳቸው ይንቁታል፤ ይዘርፉታል፤ ስርዐት አልባም ይሆናሉ። በእብሪትና በጥጋብ የተወጠሩ ታጣቂ ካድሬዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀሙ ያሉት ግድያ ስርዐት አልበኝነት በስርዐቱ እና በሃገሩ ላይ መንገሱን ይመሰክራል። ምሽት 4 ሰአት ልዮ ቦታው ቦሌ ዘ ክለብ በሚባል የምሽት መዝናኛ ክበብ አባተ አበበ የተባለ በማናለብኝነት ተስፋዬ ኦርዶፋ በተባለ ግለሰብ በ3 ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል። ገዳዩ እሳካሁን አልተያዘም።

ሟች አባተ አበበ

የሕግ የበላይነት አለመስፈኑ ፤ በአብይ አሕመድ የሚመራው አገዛዝም የዜጎችን መብት ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣኑን ወዳጅ ስለሆነ በመላው ኢትዮጵያ ሰላም እንዲደፈርስ እና ግድያዎች በባለጊዜዎች እንዲስፋፉ አድርጓል። ፍትህ ካለ ሰላም አለ አንደሚባለው ሁሉ የፍትህ ስርዐቱ ከፖለቲካ አሸርጋጅነት እስካልተላቀቀ የፍትህ አካላቱም ከፖለቲከኝነት እስካልነፁ አገዛዙም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነቱን እስካላቆመ ድረስ በሃገሪቱ አሁን ካለው ችግር በባሰ መልኩ ከባባድ የጥቃት አደጋዎችን የአፍሪካ መዲና የተባለችው አዲስ አበባ ማስተናገዷ አይቀርም።

ገዳይ ተስፋዬ ኦርዶፋ

የክልሎችን ሰላም ማስጠበቅ የተሳነው አቅመ ቢሱ አገዛዝ ጉልበቱን የሚያሳየው ተራ ያልታጠቁ ዜጎች ላይ መሆኑን ስናይ ያሳፍራል። የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የተሳነው አገዛዝ ካድሬዎቹ ራሳቸው ይንቁታል፤ ይዘርፉታል፤ ስርዐት አልባም ይሆናሉ። የአደባባይ ወንጀሎችም እንደ አሁን ቀደሞ እየተበራከቱ ይሄዳሉ። በዚህ ሰሞን የምናየው ሕገወጥነትና ስርዐት አልበኝነት የዚሁ ጉዳይ አካል ነው። ይህ በሆነበት ሁኔታ ከአገዛዙ ለውጥን መጠበቅ ሳይሆን ስር ነቀል የስርዐት ለውጥ እንዲመጣ መታገል በዋነኝነት ሊሰራበት ይገባል። #MinilikSalsawi