December 19, 2023 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደረጃጀት ጥናት ባደረጉ ተቋማትና በፀደቁ የስራ መደቦች ለመወዳደር አመልካቾች ቅድሚያ የሚሰጣቸው እውቀታቸው ወይም የስራ ልምዳቸው መሆኑን ብሄር ግዴታ ሆኖ መቅረቡ እያነጋገር ነው። በተበተነው ቅፅ 001 መሰረት አመልካቾች ብሄራቸውን እንዲሞሉና ለውጤቱ ዋነኛ መሆኑን ይህ ካልሆነ ግን አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው በቅፁ ላይ በማሳሰቢያ ተቀምጧል። እንዲሁም ለድልድሉ የሰው ሃይል መረጃ መሰባሰቢያ ቅጽ ላይ ብሄር ግዴታ መሆኑን በግልጽ መመሪያ በፅሁፍ ተላልፏል። ከታች የምትመለከቱት ሁለት የቅፆች ምስል የሚያመለክቱትም ይህንኑ ነው። የከተማ አስተዳደሩን በራሳቸው ብሄር ካድሬዎች ለመሙላት ሲባል ብቻ አመልካቾችን በብሄር በመለየት አድልዎ ለመፈጸምና ሌሎችን ብሄሮች ያገለል ቅጥር ለመፈፀም የተወጠነ መሆኑን በቂ ማሳያ ነው።

ይህ እጅግ አደገኛ የሆነ የዘር ፖለቲካ አካሄድ አፓርታይድ መሆኑ ያረጋግጣል። በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ነባር ሰራተኞችን አባሮ በኦሕዴድ ካድሬዎች ለመተካት የምዘና ፈተና በሚል ሰበብ የተጀመረው የዘር ፖለቲካ ሴራ በርካታ ሰራተኞችን ከስራ እንደሚያፈናቅል ሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ብሄር እንደ ግዴታ ቅድሚያ እንዲሰተው የተደረገውም ይህንኑ ተንኮ ለማስፈጸም እንዲረዳቸው በሚል መሆኑ ከቅፁ ማረጋገጥ ይቻላል።