December 20, 2023 – Konjit Sitotaw
የቢትወደድ መንገሻ ብርጌድ
በአንድ ሳምንት ሁለት ታሪካዊ ድል!
======================
በአንድ ሳምንት ሁለት ትንግርታዊ የአማራ ፋኖ ድል በዳንግላ የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ ተመዝግቧል። የመጀመሪያው የዳንግላ ወህኒን በመስበር ቁጥረ ብዙ የፖለቲካ እስረኞችን አስፈትቷል። በዚህ የእስረኞች መለቀቅ አዲሱ ክስተት አስገራሚው የ 18 የትግራይ ወታደራዊ መኮንኖችን ነጻ ማድረግ ብቻ አይደለም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ መሸኘትን ይጨምራል። ትልቅነት ይህ ነው! ለአማራ በየሄደበት መገደል መሰደድ እና ለዚህ ፋሽስታዊ ስርአት ዋና መስራች ህወሓት የተባለች ድርጅት ናት። የህወሓት መጨረሻ ምን እንደሚሆን ወደፊት የሚታይ ቢሆንም የሰራቸው ስርአት ግን “እሾህ ላጣሪው” እንዲሉ በዋናነት ነፃ አወጣዋለሁ ያለችውን የትግራይ ሕዝብ የጎዳ ለመሆኑ ዛሬ ነጋሪ አያስፈልግም።
የ”አረመኔው” አብይ አህመድ እና የህወሓቷ የፕሪቶርያ ስምምነት ተብየው ዳግም በአማራ ላይ ኃያላኑን ጨምሮ የተሴረበት የሁለት ዘረኞች ስምምነትን በዚህ ሳምንት የፋኖ ተጋድሎ የሁለቱ ሽውውድን አጋልጦታል። ከፍተኛ መኮንኖች ሳይቀሩ ገና በእስር እያሉ ጌታቸው አና “አረመኔው” አብይ አህመድ የጫጉላ ፌሽታቸው ሳያልቅ ህወሓት ጦርነት ያስገባቻቸው መኮነኖቿ የትም ወድቀው አሁንም የምታላዝነው ስለየመሬት ጥያቄ መሆኑ የሁለት ወንድማማች ሕዝባችንን ተፈጥሯዊ ትሥር 1983 በተሰራ ስሜታዊ ጠላትነት ልታስቀጥል መፈለጓ ነው።
ይህን በአማራ/ትግሬ የእርስ በእርስ ግጭት መቀጠል ህወሓት ብቻ ሳትሆን በይበልጥም ባለገዜው “የአረመኔው” አብይ አህመድ ኦነጋዊ መንግስትም ከነ ሌንጮ ለታ እስከ ግልገሏ ሽመልስ አብዲሳ እንደእስትራቴጅ እየተጠቀሙበት ነው። በዚህ ሳምንት ትንታጎቹ እና አእምሮ ብሩሆቹ የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ የትግራይ ወታደራዊ መኮንኖችን ከእስር በማስፈታት ወደቀያቸው መሸኘት ግን በትንሹም ቢሆን የሁለቱን ጸረ አማራ አይለወጤ ሴራቸውን ያሳብቃል። በእርግጥም እንዲህ አይነቱ ቀና ተግባር በጸረ አማራ አላማ ለተደራጁት ህወሓት/ኦነግ የሚዋጥ አይደለም። እናም የህወሓት ሚዲያወች ነገሩን አለባብሰውት አልፈዋል።
በዚህ የተበሳጨው የ”አረመኔው” የአብይ አህመድ ወታደር በታህሳስ ስምንት ቀን በታንክ እና ከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት በዳንግላ ፋኖ ላይ ለመውሰድ ተንቀሳቀሰ። የለመደበቱ ፈርጣጭ የአረመኔው ኦነጋዊ ሰራዊት በአባድራ ቱሙሀ ቀበሌወች እስከ ቆላው ወፈዲንባ ከገባ በኋላ በነዚያ የመንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ ተቀጥቅጦ ሙት እና ቁስለኛው በመኪና ጭኖ መመለሱን ሰምተናል።
ደም መላሽ የአማራ ፋኖ ብረት እንዲያነሳ የተገደደ የግፍ ጥዋ ሞልቶ በመፍሰሱ ነው። የግዜ ጉዳይ እንጅ ፋኖ እንደአያት ቅድማያቶቹ በድል አድራጊነት የአማርን እና የኢትዮጵያን እናቶች እንባ ያብሳል። ዘረኞችን ያስወግዳል።
ድል ለፋኖ!!!