የኮቪድ ዝርያ

ከ 3 ሰአት በፊት

የዓለም የጤና ድርጅት ጄኤንፖይንት ዋን (JN.1) የተሰኘው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ዓለም አቀፋዊ ስርጭቱ ፈጣን መሆኑን ይፋ አደረገ።

“በፍጥነት እየጨመረ ባለው ስርጭቱ” ምክንያት በዓለም የጤና ድርጅት ትኩረት የሚያስፈልገው ዝርያ ነው በሚልም ተመድቧል።

JN.1 የኦሚክሮን የኮሮና ቫይረስ ንኡስ ዝርያ ዓይነት ህንድ፣ ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካን ጨምሮ በብዙ የአለም አገራት ተገኝቷል።

የዓለም የጤና ድርጅት በሕዝብ ላይ ያለው አደጋ በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ መሆኑን እና አሁን ክትባቶች መከላከያ መስጠት መቀጠላቸውን አስታውቋል።

ነገር ግን ኮቪድ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በአውሮፓውያኑ ክረምት ሊጨምሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ እንደ ጉንፋን፣ የመተንፈሻ አካላት ቫይረስ (RSV) እና የልጅነት የሳምባ ምች ያሉ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶች እየጨመሩ ይገኛሉ።

ኮቪድን የሚያመጣው ቫይረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለዋወጠ በመሆኑ እና አንዳንድ ጊዜ አዳዲስ ዝርያዎችን መፈጠር ያስከትላል።

ኦሚክሮን ለተወሰነ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የበላይ የሆነ ዝርያ ነው።

ምንም እንኳን JN.1 ን ጨምሮ አንዳቸውም አሳሳቢ ናቸው ተብሎ ባይታሰብም የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በአሁኑ ጊዜ ከኦሚክሮን ጋር የተገናኙ በርካታ ዝርያዎችን በመከታተል ላይ ይገኛል።

ነገር ግን JN.1 በብዙ የዓለም ማዕዘናት በፍጥነት እየተስፋፋ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ውስጥ በጣም በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ዝርያ ነው፤ እንደ አሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል ከሆነ ዝርያው 15-29 በመቶ በሽታውን ይሸፍናል።

የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ጥበቃ ኤጀንሲ JN.1 በአሁኑ ጊዜ በቤተ ሙከራ ውስጥ ከተተነተኑት አዎንታዊ የኮቪድ ምርመራዎች 7 በመቶውን ይይዛል ብሏል። ኤጀንሲው በዚህ እና በሌሎች ልዩነቶች ላይ ያሉትን ሁሉንም መረጃዎች መከታተል እንደሚቀጥልም ተናግሯል።

የክረምት ማዕበል

JN.1 በፍጥነት እየተሰራጨ ያለበት ምክንያት ምናልባትም ስፓይክ ፕሮቲኑ ( የኮሮና ቫይረስ ወደ ሰው ልጅ ህዋስ ውስጥ የሚገባበት መንገድ) BA.2.86 ከተሰኘው ዝርያ ጋር ሲነጻጸር ተጨማሪ ልውጥ በመያዙ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ስጋት ግምገማ “ይህ ዝርያ በተለይም ወደ ክረምት አየገቡ ባሉ አገራት ላይ ሌሎች የቫይረስ እና ኢንፌክሽኖች እየተስፋፉ ባለበት ወቅት በሳርስ-ኮቭ-2 [ኮሮና ቫይረስ] የመያዝ መጠን ላይ ጭማሪ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል” ይላል።

JN.1 በክትባቶች የሚሰጠውን የመከላከል አቅም ምን ያህል ማዳከም እንደሚችል አሁንም የተገደበ ማስረጃ አለ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናግሯል።

ሰዎች ከዚህ በፊት ከነበሩት ዝርያዎች በበለጠ በዚህ ዝርያ በበለጠ ስለመታመማቸው ምንም አይነት ሪፖርቶች የሉም።

በኮቪድ ሆስፒታል የገቡትን ሰዎች መረጃ የሚዘግቡ ሀገራት ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ባለበበት ጊዜ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ነገር ግን በጤናው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስተካከል ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ብሏል።

ኢንፌክሽኖችን እና ከባድ በሽታዎችን ለመከላከል የዓለም ጤና ድርጅት ተከታዮቹን ምክር ይሰጣል-