December 21, 2023 

“ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ያለችው ህፃን በወለጋ የደረሰባትን ነገር እንዴት መርሳት ይቻላል? እንደ ህፃኗ ያሉ አማሮችን ህልውና ለመታደግ ከመታገል ሌላ ምንስ ምርጫ አለ?” ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው! ከቃሊቲ ማጎሪያ!

በወለጋ እንደ ዶሮ የታረደው በመተከል እንደ ደን የተጨፈጨፈው፣ በአጣዬ  እንደ ከሰል የነደደው የአማራ ህዝብ ፋታ በማይሰጥ የህልውና ትግል ላይ ነው፡፡

ፋሽስቱ አብይ አህመድም የአማራ ህዝብ ለህልውናው እንዳይታገል ለማድረግ በመድሀኒት መግዣና በመሰረተ ልማት መገበያያ ገንዘቦች ድሮን እየገዛና እየለመነ የአማራን መንደሮችና ሰብል ክምሮች እያወደመ ነው፡፡

መስጊዶችና ቤተክርስቲያኖች በየእለቱ እየጠፉ የአብይ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አሰቃቂ ጥፋት (የዘር ፍጅት) ጣሊያን በአምስት ዓመታት ካደረገው በላይ ዘግናኝ መሆኗል፡፡

በጥቅሉ የአማራ ህዝብ እንደ ገና ዳቦ ከላይም ከታችም እሳት እየነደደበት ይገኛል፡፡ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ እንዳለው የ1 ዓመት ከሰባት ወር ህጻን ጭምር  በድሮን ተገድሏል፡፡

ይህንን ለማድረግ ቀርቶ ለመስማት የሚዘገንን አሰቃቂ ተግባር ለመፈፀም አብይ አህመድን መሆን ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡

በጎጃም ቋሪት የ85 ዓመት ሽማግሌ በከባድ መሳሪያ ተገድለዋል፡፡ እኔ እነዚህን ለአብነት ማሳቴ እንጅ ጥቁሩ ፋሽስት (አብይ አህመድ) ሙሉ አማራን ለማጥፋት አቅዶ ሰራዊቱን አዝምቷል፡፡

ተኳሹም አራሹም ነጋሹም አማራ ግን  ህልውናውን በክንዱ ሊያረጋግጥ በ4ቱም ማዕዘናት ዝግጁ ሆኗል፡፡ አማራ እያደረገ ባለው ትግል ከታጋይ ከሚጠበቀው ዝቅተኛ መስፈርት በላይ  ጨዋነቱን እያሳም ጭምር ነው፡፡

“ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ያለችው ህፃን በወለጋ የደረሰባትን ነገር እንዴት መርሳት ይቻላል? እንደ ህፃኗ ያሉ አማሮችን ህልውና ለመታደግ ከመታገል ሌላ ምንስ ምርጫ አለ?

የአጣዬ ከተማን ከ11 ጊዜ በላይ መውደም ለማስቆም እኔ ብቻ የማውቃቸው 38 ስብሰባዎች የአብይ ፈረስ በሆኑት በብአዴኖች ተደርጓል፡፡ ነገር ግን በአጣዬ የተጀመረው የከተሞች ውድመት ቀጥሏል፡፡ አጣዬን መሰል ከተሞችን ከውድመት ለመታደግ ከመታገል ውጭ ምን ምርጫ አለ?

ምንም መታገል ብቻ!
አብይ አህመድ አሁን ላይ ሁሉንም ሰራዊት ከድንበር ጥበቃው አንስቶ ወደአማራ ክልል አዝምቷል፡፡ ይሁንና የዘመተው ሰራዊት የተሰማራው መድፍና ታንክ ለህልውና የወጣውን  የአማራን ህዝብ ሊበግረው አልቻለም፡፡

ለህውናው እየታገለ ያለውን አማራ በመድፍና በታንክ በድሮንና በጀት ማስቆም ያልቻለው የአብይ አገዛዝ ህዝቡን ለማዘናጋት ምክክርና የሽግግር ፍትሕ የሚሉ ማደናገሪያዎችን አምጥቷል፡፡

ምክክር እያለ ህዝብ ለማዘናጋት የሚሞክረው ፕ/ር መስፍን አርአያን ጨምሮ 11 ግለሰቦችን ያካተተ ኮሚሽን በማቋቋም ነው፡፡

የአማራ ህዝብ ደግሞ ከነመስፍን አርአያ ጋር ለመመካከር ይቅርና አዝመራ አጭዶ ለመከመር ወቅቶም ወደጎተራ ለማስገባት ፋታ አላገኘም ለቤተ መንግስቱ ቅርብ በሆኑና ጠቅላይ ሚኒስተሩን በሚያደንቁ ግለሰቦች የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአብይ ትእዛዝ እየተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ግን ተገማች ነው፡፡

አማራ ደግሞ በባሉም በባህሪውም ከዝንብ ማር ጠብቆ አያውቅም፡፡ ፕ/ር መስፍን አርአያ፣ አምባሳደር ማህሙድ ድፈር ፣ ዘገዬ አስፋው፣ ዶር ዮናስ    ጨምሮ እነዚህ ኮሚሽነሮች
የአማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ይቁም፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣
አዋጁ ይነሳ፣ የአብይ መከላከያ ከክል ይውጣ፣ ጦርነት ይቁም የማለት ሞራልና ብቃት አጥተው እያጭበረበሩ ይገኛሉ፡፡
ከአመራረጣቸው ጀምሮ እስካሁን ድረስ በህዝብ እየቀለዱ ይገኛሉ።

የአማራ ህዝብ እየተጨፈጨፈ ለምን ተጨፈጨፍን የሚሉትን በየእስር ቤቶቹ እየታጎሩ ባሉበት በዚህ ወቅት እንመካከር የሚል ማደንዘዣቸው  በቴሌቪዥን እየተናገሩ ነው፡፡

ፕ/ር መስፍን አርአያና ጓደኞቻቸው ለአማራ ህዝብ የምክክርና የሰላም አስተማሪ ለመሆን ብቁ አይደሉም፡፡ ይህንን የምለው ሰውዬውን በመናቅ ወይም ባለማክበር አይደለም፡፡

ይልቁንም የአእምሮ ሀኪም እንደሆኑ የሚነገርላቸው ግለሰቡ የአማራ ህዝብ ሲጨፈጨፍና ሲታረድ አእምሯቸው ዝም በማለቱ እንጅ ወዳጅም ጠላትም ማወቅና መገንዘብ ያለበት ነገር ቢኖር የአማራ ህልውና በክንዱ እንደሚረጋገጥ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ጨዋውና አስቷዬ የአማራ ህዝብ ዝግጁ ሁኗል፡፡ ስራ ላይም ነው፡፡
አማራ በደሙ ታሪክ እየፃፈ ነው!

የአራት ኪሎ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው።
ከቃሊቲ ማጎሪያ!