
“የአማራ ህዝብ ራሱን አደራጅቶ እተዋጋ ያለው የዲሞክራሲ መብቱን ለማስከበር አይደለም፡፡ ዲሞክራሲማ ለአማራ ህዝብ ቅንጦት ነው አሁን ጥርሱን ነክሶ እየተዋጋ ያለው በህይወት ለመኖር ነው።” ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
የኦሮሙማ ብልፅግና መራሹ ቡድን የአማራን ህዝብ በሠማይ እና በምድር አደኑ የገባለትን ሁሉ እየጨፈጨፈ መሆኑን አለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
የአለም ማህበረሰብ በግልፅ ያልተረዳው ግን የፋሽስቱ አብይ አህመድ አገራዊ ምክክር እና የሺግግር ፍትሕ የሚለውን ማታለያ ኢትዮጵያን ከህመሟ ሊፈውሳት ይችላል ብለው ተስፋ ለማድረግ ሲዳዳቸው ማየቴ ነው፡፡
የአማራ ህዝብ ራሱን አደራጅቶ እተዋጋ ያለው የዲሞክራሲ መብቱን ለማስከበር አይደለም፡፡ ዲሞክራሲማ ለአማራ ህዝብ ቅንጦት ነው አሁን ጥርሱን ነክሶ እየተዋጋ ያለው በህይወት ለመኖር ነው፡፡
እንደ ማህበረሰብም የራሱን ዘር ለማስቀጠልም ጭምር ነው፡፡
በሕይወት ለመኖር ዋስትና ያገኝ ዘንድ ለ30 ዓመታት ያህል ሲጠየቅ መልስ ሊያገኝ ቀርቶ ጥያቄውን ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጥ አካ አልተገኘም፡፡
አሁን እንደ ማህበረሰብ ለመጥፋት የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሲነሳ ደግሞ “ለምን ስንገድልህ ድምጽህን አጥፍተህ አልሞትክም?፣ ስናርድህ ለምን ካራውን ያዝክ?፣ ስናፈናቅልህ ለምን ዞረህ አየህ በሚል ፅንፈፈኛ የሚል ስም ተለጥፎበታል፡፡
የአማራ ህዝብ በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ሆኖ የኦሮሞ ብልጽግና የደላው ሙቅ ያኝካል እንዲሉ በአገራዊ ምክክር ጥያቄያችሁ ይፈታል በሚል ማታለያ በፈረሦቹ አማካኝነት ይዞ መጥቷል፡፡
የአማራ ህዝብ በአሁኑ ወቅት እንኳን ተሠብስቦ ለመወያየት በብልፅግና ቅጥረኛ ወታደር በግፍ የተገደለበትን ልጂን ቤተክርስቲያን ወስዶ አፈር ማልበስ አይችልም፡፡ መስጊድ ገብቶ በጀመዓ መስገድ ብርቅ ሆኖበታል፡፡
ልጆቹን ትምህርት ቤት መላክ ካቆመ ሠንብቷል፡፡ ቅጥረኛው የብልፅግና ሠራዊት ትምህርት ቤቶችንም ካምፕ አድርጓቸዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ 10 አስር ዩኒቨርስቲዎች ሙሉ በሙሉ በወታደሩ ቁጥጥር ሥር ወድቀው ተማሪዎቸን አይቀበሉም፡፡
ማሳው ጦም አድሯል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የተሰበሰበ አዝመራ በአብይ ወታደሮች ተቃጥሏል፡፡ በሬዎች ተነድተዋል ወይ ታርደዋል፡፡
ቀደም ሲል ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል፣ ከቤንሻንጉል እና በቀድሞው የደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ በትግራይ ክልል ብሎም በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ወልደው ከብደው ከሚኖሩበት ቀያቸው 5.3 ሚሊዮን አማራዎች በአማራ ክልል ቡሬ፣ ሞጣ፣በባህርዳር እና በሰከላ በጎንደር ቀበሮ ሜዳ በደብረብርሀን፣ በሀርቡ፣ በኮምቦልቻ ቃሉ፣ደጋን፣ በሀይቅ በመካነሰላም፣ በመቅደላ ማሻ፣ በመርሳ፣ በወልዲያ፣ በመቄት፣ በቆቦ እና በሀብሩ ጃራ መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡
ዛሬም ከኦሮሚያ ክልል ለመውጣት መንገድ ያጡ በየእለቱ ሞታቸውን የሚጠባበቁ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎች አሉ ይህ ሁሉ የግፍ መዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈሰሰ ነው፡፡
እንግዲህ ሀገራዊ ምክክርና ሀገራዊ ፍትሕ እየተባለ በኦሮሙማ ብልጽግና ከበሮ የሚደለቀው፡፡ ይህ ድለቃ እንኳን የአማራን ህዝብ ከሞት ሊያድነው የእኔ ነው የሚለውን የኦሮሞን ህዝብ አንድ ስንዝር እንኳን አያራምደውም፡፡
በእርግጥ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ለማታለል ይጠቀምበታል፡፡ የተወሰነ ድጋፍና ብድርም ያገኝበት ይሆናል፡፡ የዋህ ምሁራንም እንደፈረስ መጋለቢያ ኮርቻም ይጠቀምባቸዋል፡፡ ከዚህ የተለየ ግን ጠብ የሚል ነገር እንደማይኖረው የአማራ ህዝብ የሚያውቀው ነው፡፡
ይሁን እንጅ የአብይ አህመድ ፈረሶች በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ህዝብ ለሚወያይበት በሚል ወደ ወረዳና ቀበሌዎች በቅጥረኛ ወታደሮች ታጅበው በመሽሎክሎክ ህዝብን እያደናገሩ ይገኛሉ፡፡
በየአካባቢው ያለው የአማራ ፋኖ ይህንን ተረድቶ ፈረሶቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድባቸውና የአማራን ህዝብ ለማያባራ ስቃይ የሚዳር የኦሮሙማ ብልፅግና ፈረሶችን እንዲያፀዳ ስል እጠይቃለሁ፡፡
የአማራ ድምፅ ሚድያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
ከቃሊቲ ማጎሪያ!