አስደናቂ አስደማሚ ኦፕሬሽን በቡሬ ተፈፅሟል
ይህ ዜና ለመተኛት ለምትሰራዱ የመልካም ሌሊት፣ ቀናችን ለምትጀምሩ ደግሞ የብሩህ ቀና ዜና ይሁንልን።
ቡሬ ከተማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ መሽጎ የነበረው የጠላት ኃይል ዙ -23 እና ሞርታር በመያዝ በካምፑ የተወሰነ ኃይል አስቀርቶ ግዳጅ ተሰጥቶት ወደ ሽንዲ ከተማ ከተማ ይሄዳል፤ ሌላ 2 ሲኖትራክ ኃይል ደግሞ ድጋፍ ለመስጠት በካምፑ ውስጥ ለጉዞ ተዘጋጅቷል።
ይኸኔ ኦፕሬሽን ነድፎ ይጠብቅ የነበረው መቶ አለቃ ኢንጅነር ዘመኑ አማረ ስር ያለው የዳሞት ብርጌድ የአሳምነው የሻለቃ ታህሳስ 11/2016 ዓ.ም ማታ 2:00 ወደ ካምፑ ዘልቆ በመግባትና ጥቃት በመክፈት ዋርድያን ጨምሮ ካምፕ ውስጥ የነበረውን አራዊት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በ25 ደቂቃ ውስጥ መደምሰሱ ታውቋል።
በዚህ ኦፕሬሽንም ጀግናው የዳሞት ብርጌድና ሻለቃ ብሬን፣ መትረጊስ፣ የነፍስ ወከፍ ክላሽ፣ ተተኳሽና የምግብ ሬሽኖችን (ብስኩት እና አስቃፅላ) የላከላቸውን ከአሰላው የአህያ ቄራ ያመለጠውን ብርሃኑ ጁላን አመስግነው ገቢ ማድረጋቸው ታውቋል።
በዚሁ ኦፕሬሽን ባህርዳር ዊክሊክስን እጅግ ያስደሰተው ነገር ደግሞ ከሰሞኑ እዛው በቡሬ ከተማ መስጅድ ውስጥ ገብተው አንድን ሼክ ከገደሉት ውስጥ የነበሩ የአገዛዙ ታጣቂዎችም አብረው መደምሰሳቸውን መስማታችን ነው።
ከድሉ በኋላም እነ መቶ አለቃ ኢንጅነር ዘመኑ አማረ ለሚሊሽያ፣ ለፖሊስና ለሰራዊቱ አባላት እስከ ታህሳስ 30 ድረስ የእጅ ስጡ ጥሪ ወረቀት ካምፓቸው ውስጥ በትነውላቸው በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል። መቶ አለቃ ኢንጅነር ዘመኑ አማረና ጓዶቹ እየከፈላችሁት ስላለው የተግባር መስዕዋትነት ትልቅ ትልቅ አክብሮት አለን።
አሻራ ሚዲያ