
23 ታህሳስ 2023, 08:24 EAT
ዩክሬን እአአ ከ1917 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የገና (ልደት) በዓል የሚከበርበትን ቀን ለወጠች።
በጎርጎሮሳውያን ቀን አቆጣጠር መሠረት ዩክሬን ገናን በታኅሳስ 25 ለማክበረው ነው የወሰነችው።
ከዚህ ቀደም ግን የጁልያን ቀን አቆጣጠርን በመከተል በዓሉ በጥር 7 ይከበር ነበር።
ዩክሬን፣ የኢትዮጵያ ገናም ከሚከበርበት ታህሳስ 29 በዓሉን ወደ ታህሳስ 25 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ታህሳስ 15 ለማዞር የወሰነችው ከሩሲያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ነው።
በዩክሬን ያለው የባህል ለውጥ ማሳያ ነው ተብሏል።
ሞስኮ በዩክሬን ላይ ያላትን ጫና ለማጥፋትና ምዕራባዊውን የጎርጎሮሳውያን ቀን መቁጠሪያ ለመከተልም ዩክሬን ወስናለች።
በዩክሬን፣ ከኪዬቭ ውጭ የሚገኘው ገና ዛፍ ማስዋቢያ ማምረቻ በሶቭየት ኅብረት አሉ ከሚባሉ ሦስት ፋብሪካዎች አንዱ ነበር።
በዚህ ፋብሪካ የምትሠራው ሊዮካዳ እንደምትለው ቀድሞ ብዙ ደንበኞች የነበሯቸው ቢሆንም አሁን ተቀዛቅዟል።
ከ1978 ወዲህ በዚህ ፋብሪካ ውስጥ ሠርታለች።
ለዓመታት የግብዓት እጥረት ገጥሟቸው ቆይተው የሩሲያ ኃይሎች አካባቢውን ሲቆጣጠሩ ማምረት አቋረጡ።
ሌላዋ ሠራተኛ ሄንያ “ታንኮች ከተማ ውስጥ ሲገቡ አስፈሪ ነበር። መውጣት አልቻልንም። መረጃም አናገኝም ነበር። ከዓለም ተቆራርጠን ነበር” ብላለች።
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ ሠራተኞች ብቻ ቢኖሩም የገና ዛፍ ማስዋቢያ በጥቂቱ ማምረት ቀጥለዋል።
ሄንያ በሩሲያ ኃይሎች ይዞታ ሥር ያሉ አካባቢዎች ነዋሪዎች “ነጻነት ይመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ትላለች።
- በርካቶች ካናዳን ለመኖሪያነት ለምን ይመርጧታል?23 ታህሳስ 2023
- ‘ሆሊውድ ለኔ ሀብትና ትምህርት ቤቴ ነው’ – ፍርቱና ገብረስላሴ23 ታህሳስ 2023
- ከመርዛቸው መድኃኒት ለመቀመም ከ50 በላይ የእባብ ዝርያዎችን የሚያረባው ማዕከል23 ታህሳስ 2023
ዩክሬን እና ሩሲያ ብዙ የሚያመሳስሏቸው ባህሎች አሉ።
ከጦርነቱ በኋላ ግን ይሄ ትስስር ላልቷል።
ቡቻ በሚባለው የዩክሬን አካባቢ ይህ ጎልቶ ይታያል።
ሩሲያ ወደ ዩክሬን መዲና ስትጠጋ 500 ንጹኃን ዜጎችን በመግደል ተከሳለች።
ሴንት አንድሪው በተባለ ቤተክርስቲያን ከተገደሉት ሰዎች የተወሰኑት ስም ዝርዝር ተለጥፏል።
በዚህ አካባቢ የጅምላ መቃብርም ተገኝቷል።
በቤተክርስቲያኑ የሚያገለግሉት አባት አንድሪ “በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙዎች ዩክሬንን ከሩሲያ ጋር አስተሳስረው ያስቧታል። እኛ ግን የአውሮፓ ጎረቤትነታችን ይበልጥብናል” ይላሉ።
“ቀን መቁጠሪያ ስንቀይር ከሩሲያ እየራቅን ሳይሆን ወደ አውሮፓ እየቀረብን ነው። ፈጣሪ ከተፀፀቱ ወራሪዎችንም ይቅር ይላል። ሩሲያውያን ግን አልተፀፀቱም” ብለዋል።
ለዩክሬናውያን ሩሲያ ጦርነቱን ስታቆም ነው ይቅር መባባል ሊጀመር የሚችለው።
ይህ እንደሚሆን የሚያሳይ ምልክት ግን የለም።