
Saturday, 23 December 2023 20:53
Written by Administrator

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ይህ ህክምና የተደረገላት ታካሚ ከአዲስ አበባ በጥቂት ርቀት ላይ የምትኖር ሲሆን፤ ድንገት በዕለት ሥራዋ ላይ ሳለች ከፍተኛ የራስ ህመም ይሰማት እንደጀመረና ከዚያም እራስዋን ስታ መውደቋን ታሪኳ ያስረዳል።
ህክምና ተቋም እንደደረሰችም በተደረገላት ምርመራ በአንጎልዋ ውስጥ የደም ቧንቧ መፈንዳት ምክንያት የደም መፍሰስ እንደተከሰተና የፈነዳው የደም ቧንቧ በቀዶ ጥገና ህክምና ባስቸኳይ ካልተስተካከለ ለሞት የሚዳርጋት መሆኑን ይነገራታል።
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኒውሮሰርጀሪ ዲፓርትመንት አስተባባሪነትና የአንጎል ደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ህክምና ከፍተኛ ልምድ ባካበቱት ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ የሚመራ የህክምና ቡድን፣ ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሶስት ሰዓት ከግማሽ በወሰደ የቀዶ ጥገና፣ የተስተካከለ የአንጎል የደም ዝውውር እንዲኖራት ማድረግ ተችሏል።
ታካሚዋ በተደረገላት ህክምና እጅጉን እንደተደሰተች ገልጻ፥ ባሁኑ ሰዓት ከህመምዋ አገግማ ወደ ቤትዋ ተመልሳለች፡፡ ይህ ህክምና ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ በመንግስት ሆስፒታሎች ሲሰራ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።