December 25, 2023 – Konjit Sitotaw 

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሃላፊ አብዱል ካማራ ላይ በምሽት ከቢሯቸው ውጭ አካላዊ ድብደባና እስር የፈጸሙት የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚንስትር ጠባቂዎች መኾናቸውን ሰምቻለሁ ሲል ደይሊ ኔሽን ዘግቧል።

የድብደባውና እስሩ ምክንያት፣ መንግሥት ለባንኩ መክፈል ያለበት 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ መዋጮ ለባንኩ እንዳልደረሰ የባንኩ ሃላፊዎች በመግለጣቸው እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። ሌላኛው ታስረው የተደበደቡት፣ የባንኩ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ሃላፊ ቦስኮ ቡከንያ ናቸው ተብሏል።

ኾኖም ገንዘብ ሚንስቴር አቢጃን ለሚገኘው የባንኩ አካውንት ሳይኾን፣ በባንኩ ኢሜል ስም በተላከለት ሌላ ሜክሲኮ ወይም ፓናማ ለሚገኝ የባንክ ሒሳብ 6 ሚሊዮን ዶላር ስለመክፈሉና መንግሥትም በጉዳዩ ላይ ምርመራ ስለመጀመሩ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።

ቡከንያ ወደ ቤታቸው ተወስደው ቤታቸው እንደተፈተሸና ላፕቶፖችና ደረሰኞች እንደተወሰዱባቸው ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።