በቀን 12/04/2016 ዕለተ አርብ ከምሽቱ 12:30 እኔ የማሽከረክረው ላንድ ሮቨር መኪና ታርጋው ኦሮ የሆነ እኔና የኔ እንግዶች የሆኑ ሶስት የመንግስት አካላት ባሉበት ስንጓዝ በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ ከአቶቴ ወደ ፉራ በሚወስደው መንገድ ቦሌ መንደር የሚባለው የትራፊክ መብራቱጋ ስንደርስ የማሽከረክረውን መኪና ከጎን በኩል በመጠጋት በከፍተኛ ምት ይመቱታል። እኔም አደጋ የደረሰ ስለመሰለኝ መኪናውን ዳር በማስያዝ በማቆሜ አንደኛው ከመኪና ፈጥኖ በመውረድ የተመታውን መኪና ዙሪያውን ቢመለከት የደረሰ አደጋ ባለመኖሩ ከመኪናው ሁዋላ የተሰበሰቡትን ወጣቶች የደረሰውን ግጭት ምንነት እየጠየቃቸው እያለ ነበር እኔም ከመኪናው በመውረድ ወደ ወጣቶቹ በመሄድ ምን ተፈጠረ በማለት የጠየቅነው

በዚህ ፍጥነት ከአስፓልቱ ዳር ከሚገኝ ሁለት ፑል ቤት አንድ ግሮሰሪ ተጨማሪ ወጣቶች ከበቡን ወዲያው አንድ ወጣት በተለምዶ በአከባቢው አጠራር #ባንጋ የተባለ ሳንጃ ይዞ እኛን ማሳድ ያዘ። በሁኔታው በመደናገጣችን ብናፈገፍግም ሊተወን ባለመቻሉ ወደ መኪናው ሸሸን በዚሁ ጊዜ ነበር ወጣቶቹ እኛ ወደ መኪናው እንዳንገባ በሩን የያዙብን።
ሁኔታው በተደራጀ መልኩ ዘረፈ መሆኑ ስለገባን በሳንጃው ላለመወጋት መሸሽ ጀመርን ። በዚህ መካከል ያልወረዱት ከመኪና እንዳይወርዱ መኪናውን ሎክ ለማድረግ ብሞክርም ከሁዋላ በር በመክፈት ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣና ከአንድ ፕሮግራም ቀረፃ እየተመለስን በመሆኑ ብላክ ማጂክ ካሜራ ፣ መቅረፀ ድምፅ የያዘ ቦርሳ ይዘው ተሰወሩ።
ሁላችንም እራሳችንን በማትረፍ ተጠምደን ስለነበር የአከባቢው ማህበረሰብና ነጋዴው ማህበረሰብ ዘራፊዎቹ ከአከባቢው መሰወራቸውን በመመልከት ከበውን ስፍራውን ቶሎ ለቃችሁ ካልሄዳችሁ አሁን ከመጡ ይገሉአችኋል በማለት አከባቢውን ለቀን እንድንሸሽ ያስፈራሩን ጀመር ።
ሁኔታው በተጠናና በከፍተኛ የዘረፋ ኦፕሬሽን የተሰራ በመሆኑ ከአከባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ አለነበርንም። የፓሊስ አካል እስኪመጣ ስፍራውን ላለመልቀቅ ወሰንን። በዚህ መካከል አንድ የፓሊስ አባል የመጣ ሲሆን ቀርቦ ምንድነው ሲል ጠየቀን
እኛም የደረሰብንን የዘረፋና ወንጀልና የግድያ ሙከራ አስረድተን የህግ ከለላ ብንጠይቅም ፓሊሱ በቃ አሁን ከዚህ ሂዱ ልጆቹ ከላልታወቁ ምን ማድረግ ይቻላል በማለት ሲመልስልን

ቢያንስ ፓትሮል ደውሎ ሀይል እንዲያስጨምርልን ብንነግረውን እኔ የናንተ ጠባቂም ተላላኪም አይደለሁም ሲል የመኪናውን ታርጋ ዞሮ ከተመለከተ በሁዋላ እኔን ለመምታት የለበስኩትን ሸሚዝ በመያዝ አነቀኝ።
ከዚህ በሁዋላ ጉዳዩ ከአቅም በላይ እየሆነ በመሆኑ የፓሊስ አካልም የህግ ከለላ እንዳልሰጠን ስናውቅ ወደ አንድ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ዘንድ ደውለን እንዲደርሱልንና የደረሰብንን በደል ብናስረዳም ከባለስልጣኑ ዘንዳ ምንም አይነት እርዳታ ባለማግኘታችን። ወደ ተለያዩ የህግ አካላት ደወወለን ከ40 ደቂቃ በሁዋላ አንድ የፓሊስ ፓትሮል መጣልን።
የመጡት የፓትሮል አባላት በተወሰነ መልኩ ሊሰሙን የሞከሩ ቢሆንም እነዛ ዘራፊዎችን ስማቸውን እና አድራሻቸውን እኛኑ ከመጠየቅ ግን አልቦዘኑም።
እኛ መንገደኛ ስንሆን እንዴት የዘራፊዎቹን ማንነት በስምና በአድራሻ ለይተን ለፓሊስ መናገር እንደምንችን ስላልገባን ቢያንስ የተወሱ ወጣቶች የወጡበትን ግሮሰሪና ፑል ቤት ያሳየን ሲሆን ከከፍተኛ ክርክርና አለመግባባት በሁዋላ ፓሊሶቹ የዕለት መዝገብ ላይ እንድናስመዘግብ ወደ ታቦር ክፈለ ከተማ ፓሊስ ማዘዣ ጣብያ መኪናችንን እያሽከረከርን ሄድን።
በዚህ መሃል የፑል ቤቱ ባለቤቶች አንዳንድ ነገር ሲናገሩ በመስማታቸው ፓሊሶቹ አስረዋቸዋል።
ነገር ግን ዋና የተደራጁትን የዘራፊ ቡድኖች የያዘም ሆነ በወቅቱ ለመከታተል የሞከረ አካል የለም።
ልብ በሉ ሀዋሳ ከምሽቱ 12:30 ማለት ቀን ነው ።
ሰው በዚያ ወቅት መንገድ ላይ በብዛት ይታያል። ነገር ግን በጣም የተደራጁ ወጣቶች በማን አለብኝነት የሚሽከረከር ተሽከርካሪን በማስቆም በሣንጃ እና በሌሎችን ድምፅ በሌላቸው ጎጅ መሳሪያዎች በመታገዝ ዘረፋ ሲፈፅሙ በአከባቢው ዘራፊዎቹን ሊጠቁምም ሆነ ለመያዝ የሚተባበር አካል ማጣት ሀዋሳ ወዴት እየሄደች ነው ያሰኛል።
አሁን ጉዳዩ በፓሊስ የተያዘ ቢሆንም ዛሬም በዚያው ቦታ ዘረፋ እንደተፈፀመ ሰምተናል።
ሀዋሳ ተወዳጅ እና በብዙሃን ኢትዮጵያውያን ተመራጭ የመዝናኛ ከተማ ስትሆን እንዲህ አይነት በጠራራ ፀሃይ ዘረፋ ሲፈፀምና እና አስፓልት ላይ ግድያ ለመፈፀም ሲሞር የፓሊስ አካል አስቸኳይ ግብረ ሀይል በማቋቋም ወንጀለኞችን ለመያዝ ፈጣን ጥረት ባለማድረጉ አዝነናል።
ይህ ወንጀል በአስቸኳይ ተጣርቶ የፓሊስ አካልም ሆነ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ወልጀለኞችን በማደን ከወንጀል የፀዳች ሀዋሳን እንደሚያሳየን ተስፋ አለን።
እሰወከዛው ጉዳዮን የሚለከተው የክልሉም ሆነ
የፌደራል መንግስት ጉዳዮን በማሳወቅ ህጋዊ አቅጣጫ ተከትለን ሄደናል። Yerassew Gezahegn