
ከ 9 ሰአት በፊት
የክሬምሊን ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫሊኒ በሕይወት እንዳሉ እና በሰርቢያ የወንጀለኞች ማቆያ እንደሚገኙ ቃለ አቀባያቸው አስታውቀዋል።
ቃለ አቀባያቸው ኪራ ያርምሽ “አሌክሲ ናቫሊኒን አገኘነው” ሲሉ በሰሜናዊ ሩሲያ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ተቃዋሚው አስቀድሞ ከነበሩበት እስር ቤት ከተዘዋወሩ በኋላ ባልደረቦቻቸው ከአውሮፓውያኑ ታህሳስ 6 ጀምረው እንዳላገኟቸው ታውቋል።
የቭላድሚር ፑቲን ቀዳሚ ተቃዋሚ የሆኑት አሌክሲ ናቫሊኒ ከአውሮፓውያኑ 2021 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ።
“ጠበቃው ዛሬ አግኝቶታል። አሌክሲ ደህና ነው” ሲሉ በቴሌግራም የትስስር ገጽ ጽፈዋል።
በሰሜን ሩሲያ ካርፕ ‘አይኬ-3’ ወደ ተባለ የወንጀለኞች ማቆያ ግዛት እንደተዛወሩም ተናግረዋል።
አሌክሲ ናቫሊኒ ከዚህ ቀደም ከሞስኮ 235 ኪ.ሜ ርቀት በሚገኘው ሜልኮቮ ታስረው ነበር።
አሜሪካ ናቫሊኒ ያሉበት ቦታ መታወቁን የሚያሳዩ ሪፖርቶችን በደስታ መቀበሏን ብታስታውቅም፤ የተቃዋሚው ደህንነትና አያያዝ “በእጅጉ እንደሚያሳስብ” ገልጻለች።
አዲሱ እስር ቤት በሩሲያ አደገኛ ከሚባሉ እስር ቤቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይታመናል። አብዛኞቹ ታሳሪዎችም በከባድ ወንጀሎች የተፈረደባቸው ሰዎች ናቸው።
ቃል አቀባይ ኪራ ያርምሽ የሩሲያ ባለስልጣናት ናቫሊኒን ለመነጠል ፍላጎት አላቸው ያሉ ሲሆን፤ ህይወቱን እስከመጨረሻው ድረስ ከባድ ለማድረግ እየሞከሩ ነው ብለዋል።
- እስራኤል በጋዛ ላይ እያደረሰችው ያለው የአየር ጥቃት እረፍት የለውም- ተመድ26 ታህሳስ 2023
- እስራኤል በሶሪያ በፈጸመችው ጥቃት የኢራን የጦር አዛዥ መገደሉን ኢራን አስታወቀች26 ታህሳስ 2023
- “ቦምብ ሲወድቅብን ለልጄ ‘አክሽን ፊልም ነው’ አልኩት”26 ታህሳስ 2023
“አካባቢው በጣም ሩቅ ነው፤ ለማግኘት ከባድ ነው። ለጠበቃዎች ሄደው አሌክሲን ማየት በጣም ከባድ ነው የሚሆነው” ሲሉ አክለዋል።
የናቫልኒ ረዳት ኢቫን ዛዶቭ የእስር ቤት ዝውውሩ “ስርዓቱ የፖለቲካ እስረኞችን እንዴት እንደሚይዝና ለመነጠልና ለመጨቆን የሚያደርገውን ሙከራ” ያሳያል ብለዋል።
ታዋቂው ተቃዋሚ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ባለመቅረባቸው ባልደረቦቻቸው ጭንቀት ላይ ነበሩ።
አሌክሲ ናቫሊኒ በጸረ ሙስና ዘመቻቸው ዝና ማፍራት የቻሉ ሲሆን፤ የምርመራ ቪዲዮዎቻቸው የሚሊዮኖችን አይን መሳብ ችለዋል።
በመላው ሩሲያ በጸረ መንግስት ተቃውሞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ህዝቦች በመቀስቀስ ብቸኛው የሩሲያ ተቃዋሚ ሳይሆኑ አይቀሩም።
ነበር ግን እ.አ.አ በ2020 በሰርቢያ ‘ነርቭ ኤጀንት’ በተባለ ኬሚካል ተመርዘዋል።
በውጭ ህክምናቸውንም ተከታትለዋል።
አሌክሲ ናቫሊኒ በ2021 ወደ ሩሲያ ሲመለሱ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል።