(ጌታቸው ሺፈራው)

News Feed posts
የዐቢይ አህመድ፣ ኦነግ፣ ሜጫና ቱለማ በአማራው ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ(ጌታቸው ሺፈራው)አንድን ተቀናቃኝ ኃይል ለማዳከም ጠንካራና ደካማ ጎኑን መለየት የመጀመርያው ስራ ነው። ባላንጣው መሰረቱን ለመናድ ያስችላል ያለውን ጠንካራ ጎን ለመጉዳት ይጥራል። ሰሞኑን በአማራው ላይ እየተፈፀሙ ካሉት ጉዳዮች መካከል አንዳንዶቹን ብናይ ይህን የባላንጣዎች ተግባር እናገኘዋለን።የኦነግ መሰረት የሆነው ሜጫና ቱለማ የሚባል ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ተስፋፊዎች ቤተ አማራ/ወሎ ድረስ የሚለጥጡትን ካርታ በባነር ሰቅሎ አሳይቷል። ከሳምንት በፊት የሜጫና ቱለማ ውላጅ የሆነው ኦነግ የተባለ የፅንፈኞች ድርጅት “ወሎ የኦሮሞ ግዛት ነው” ብሎ መግለጫ ሰጥቷል። ሁለቱም የለየላቸው ፅንፈኛ ተቋማት ናቸው። የጥላቻ ተቋማት ናቸው። ሁለቱ ድርጅቶች ግን የተወጡት የተለያዩ ሚና ነው። ኦነግ በመግለጫው ቃል በቃል ቤተ አማራ/ወሎን የኦሮሞ ግዛት ነው አለ። የኦነግ መመልመያና መፍለቂያው ሜጫና ቱለማ ደግሞ ካርታውን አሳይቶ ከኦነግ አነስ ያለ የመሰለ የፅንፈኝነት ሚናውን ተወጥቷል።የኦሮሞ ፅንፈኛ ድርጅቶች አቋም የተለመደ ነው። የስግብግብነትና የመስፋፋት አባዜ የተጠናወታቸው ናቸው። የሚገርመው የሁለቱን ፅንፈኛ ድርጅቶች አቋም አነስ ባለ በሚመስል ነገር ግን አደገኛ በሆነ ተግባቦት ለመወጣት የሚጥረው መንግስታዊ መዋቅር ነው። የፅንፈኞችን አላማ የተጋራው በቀን አስር ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲያወሳ የሚውል ሰው መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን የባሰ አሳፋሪ ያደርገዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ያደረጉትን እጅግ አስነዋሪ ንግግር መጥቀስ ይቻላል።ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሰኔ 8/2011 ዓም ወደ ቤተ አማራ/ወሎ አቅንተው ነበር። ይህ የሆነው ኦነግ “ወሎ የኦሮሞ ግዛት ነው” ብሎ መግለጫ ካወጣ ከሳምንት በኋላ ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ቤተ አማራ ያቀኑት ሜጫና ቱለማ የተባለው የኦነግ መሰረት የሆነ ድርጅት ቤተ አማራን የኦሮሚያ አካል የሚያደርግ ካርታ የታተመበት ባነር ሰቅሎ መግለጫ የሰጠ ሰሞን ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ቤተ አማራ መሄዳቸው ችግር አልነበረውም። በስብሰባው ወቅት የተናገሩት ግን ከኦነግና ከሜጫና ቱለማ ጋር የሚያስማማቸውን አቋም ማራመዳቸው፣ የፅንፈኞቹን አላማ አንግበው የሄዱ መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ቤተ አማራ/ወሎን እንደ አንድ ማንነት አድርገው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተሰምተዋል። ቤተ አማራ/ ወሎን ከአማራ ማንነት ነጥለው በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ጭራሽ ቤተ አማራ ከአማራ ማንነት ተለይቶ የአማራና የትግራይ እንዲሁም የኦሮሞና የአማራ ድልድይ የሆነ የተለየ ማንነት ያለው አስመስለው እጅግ አሳፋሪ አቋም አንፀባርቀዋል። የጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ ይህን አቋም ሲያንፀባርቁ ሆን ብለው መሆኑን የውይይቱን ቪዲዮ ያየ ሁሉ የሚገነዘበው ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ይህን አቋም ሲይዙ ብቻቸውን አይደለም። ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የተባበሩበት አውድ ይታያል። ኦነግ ቤተ አማራ/ወሎን የኦሮሞ ግዛት ነው ባለ በሳምንት ውስጥ፣ የኦነግ መነሻ የሆነው ሜጫና ቱለማ ቤተ አማራ ድረስ የሚደረሰውን የተስፋፊዎች ካርታ ዘርግቶ መግለጫ በሰጠበት ሰሞን ቤተ አማራን ከአማራ ነጥለው የአማራና የሌሎች ድልድይ የሆነ የተለየ ማንነት ያለው ለማስመሰል የጣሩት ጠ/ሚ ዐቢይ የተወጡት ሶስተኛ ሚና ነው። ኦነግ በግልፅ የአማራው ዋና እምብርት የሆነውን ቤተ አማራን የኦሮሚያ ግዛት ነው አለ። ኦነግ የወጣበትና ራሱን ሲቪክ ማኅበር ነኝ የሚለው ሜጫና ቱለማ ኦነግ በመግለጫው ኦሮሞ ነው ያለውን ቤተ አማራ ካርታ ወደ ኦሮሚያ አጠቃልሎ በሚዲያ አሳየን። ሜጫና ቱለማ ከኦነግ ለስለስ ባለ መልኩ ተስፋፊነቱን ሲገልፅ መንግስት የሚባለውን የሚመሩት ጠ/ሚ ዐቢይ ደግሞ የአማራውን እንብርት ቤተ አማራን ከአማራ የተነጠለ ማንነት እንዳለው አስመስለው አሳፋሪ የሆነ አቋማቸውን ሲገልፁ ውለዋል።የሶስቱ ኃይሎች አላማ ግልፅ ነው። ሚናቸውም የተቀናጀ ነው። የመንግስት ግዴታ አለብኝ ያሉት ሰው የአማራው አንጓ የሆነውን ቤተ አማራ ከአማራነት ማንነት ነጥለው ለማሳየት ሞከሩ። ሲቪክ ማሕበር ነኝ የሚለው ሜጫና ቱለማ ካርታውን ስሎ በሚዲያ አሳየ። ከሜጫና ቱለማም የለየለት ፅንፈኛው ፀረ አማራ ኦነግ የተባለ ድርጅት የአማራውን አንጓ፣ ቤተ አማራን የኦሮሞ ግዛት ነው ብሎ ከጠ/ሚ ዐቢይም ከሜጫና ቱለማም ላቅ ያለና የለየለት አቋሙን ገልፆ መግለጫ ሰጠ። የሶስቱ አካላት ልዩነት የሚና መለያየት ነው። ፕሮፖጋንዳቸው የተለያየው በታክቲክ ብቻ ነው። አንደኛው ለጣራ ሲጠይቅ ሌላኛው ከዛም ከፍ ላለ፣ ሌላኛው ለሰማይ ይጠይቃል። ሁሉም ኃይሎች አንድ አላማ አላቸው ቤተ አማራን ከአማራው በመነጠል የአማራውን አንጓ መምታት ነው።በተለይ የአማራ ብሔርተኝነት ሲጠነክር እንደነ ዐቢይ አህመድ የደነገጠ ያለ አይመስለኝም። ጠ/ሚ ዐቢይ ትህነግ/ሕወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የወልቃይት ጥያቄ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ነው ሲሉ ተቃውሞ ገጠማቸው። ወደ ጎንደርና ባሕርዳር በመሄድ የአማራውን አቋም አለሳልሰው ለመመለስ ጥረት አደረጉ። ያዩት ግን ማመን ያልሉትን ብሔርተኝነት ነው። አማራው አዳራሽ ውስጥ ቀልድ ስለቀለዱለትና የማይጨበጥ ተስፋ ስለሰጡት ብቻ ሽብርክ የሚል እንዳልሆነ ሲያውቁ ሌላ እቅድ ነደፉ። የመጀመርያው ከአማራው አብራክ የወጡትን ለዘብተኛ አቋም የያዙ ታዋቂ ግለሰቦች በመላክ ለማቀዝቀዝ ጥረዋል። እነዚህ ግለሰቦች ውጤታማ መሆን አልቻሉም። ሁለተኛው እቅድ የአንድነት ኃይል ነን የሚሉትን ድርጅቶች መጠቀም ነው። ይህኛውም ውጤታማ ሊሆን አልቻለም። በሶስተኛ ደረጃ በጎጥ ማሕበርና በእምነት ስንጥቅ ለመፍጠር የተጣረ መሆኑንም የምናጣው አይደለም። በአራተኛ ደረጃ አዴፓ/ብአዴን የአማራውን ንቅናቄ እንዲያቀዘቅዝ ማዘዝ ነው። ይህኛውም እስካሁን ቀላል አልሆነም። ለአዴፓ/ብአዴን ከአማራው ንቅናቄ ጋር የመላተምን ያህል ራስን የማጥፋት ተግባር ያለ አይመስልም። ይህን አዴፓም የሚረዳ ይመስላል። በእርግጥ ይህን የእነ ዐቢይ ተልዕኮ ለመወጣት የሚጥርበት አጋጣሚ የለም ማለት ይከብዳል። ግን አጥጋቢ የሆነላቸው አይመስልም። አምስተኛው አማራጭ የለየለትን አቋም መውሰድ ነው። ከኦሮሞ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ሚና ለይቶ በአማራው ላይ መዝመት ነው። ሰኔ 8/2011 ዓም ጠ/ሚ ዐቢይ ያደረጉት እጅግ አስነዋሪ ንግግር የሚያስረዳው ከኦሮሞ ፅንፈኞች ጋር በመተባበር የአማራውን አንጓ ለመምታት ሚና መከፋፈላቸውን ነው። ከወራት በፊት ቤተ አማራ ወሎ አካባቢ ለተደረገው ጥቃት የኦሮሞ ኃይሎች እጅ እንደነበረበት ግልፅ ነው። ለዚህ ደግሞ የገዥውና ዐቢይ የሚመሩት ድርጅት እጅ የለበትም ለማለት አይቻልም። ምድረገኝ/ከሚሴ ውስጥ ሽብር የፈጠሩ አመራሮች ከታሰሩ በኋላ የኦሮሞ ኃይሎች ተቀናጅተው አዲስ ጥቃት ለመፈፀም እቅድ ነበራቸው። ለጊዜው ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ ኃይሎች በአማራው ላይ ያደረጉትን ቅስቀሳ በጆሮዬ አዳምጫለሁ። የኦሮሞ ኃይሎች ጉዳዩን ወደሚዲያ ለመጎተት ያደረጉትን ጥረት አይተናል። ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ የታሰሩት ይፈቱ እያለ የሚወተውት የኦሮሞ ገዥ ድርጅት መዋቅርም እንዳለ እየተገለፀ ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ደሴ በሄዱበት ወቅት ይህን አጀንዳ አያነሱም ማለት አይቻልም። አማራው የሚጠቃባቸው ስስ ክፍሎች በኩል እሳት ሲጫር ቆይቷል። አንደኛው ምደረገኝ ነው። በየቦታው እሳት ሲያቃጥል የከረመው ማን እንደሆነም እስከመቸውም ተደብቆ የሚቀር አይደለም። የአማራው አንደኛውና ጠንካራው አንጓ ቤተ አማራ ነው። ስስ በሆነው በምድረገኝ በኩል እሳት ለመለኮስ የጣሩት ሲያዙ የኦሮሞ የፖለቲካ ቡድኖች ዋናውን ቤተ አማራን፣ የአማራውን አንጓ ለማጥቃት የተለያየ ሚና ወስደው ዘምተዋል። መንግስት የሚባልን የሚመሩት ዐቢይ አህመድ ቤተ አማራን ከአማራ ለመነጠል ያስችላል ያሉትን ንግግር ሲደጋግሙ ዋሉ። ሲቪክ ማኅበር ነኝ የሚለው ካርታውን ዘርግቶ መግለጫ ሰጠ። ከሁለቱም የባሰው ኦነግ አፉን ሞልቱ “ወሎ ኦሮሞ ነው” አለ። ይህ የስስቱ ትብብር በአማራው ላይ የተቃጣ ነው፣ ባላንጣነት ነው። ዐቢይ አህመድ፣ ኦነግ እና ሜጫና ቱለማ!
Like
Comment
Share