” ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበል የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው ” – መምህራን
በመቐለ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ፤ ” 17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም ” ብለው የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።
ተማሪ ሄመን ሰለሙን በመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የሓየሎም መለስተኛ ትምህርት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፤ ታህሳስ 13 /2016 ዓ.ም በትምህርት ቤትዋ የወላጆች በዓል ከተከበረ በኃላ ከትምህርት መአድ መስተጓጎሏን ተናግራለች።
ምክንያቱ ደግሞ የትምህርት ቤትዋ መምህራን ” 17 ወራት ዉዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም ” ብለው የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ነው።
የተማሪ ሄመን ሰለሙን አስተያየት በመቐለ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይጋሩታል።
ተማሪዎቹ ትምህርት ካቆሙ ቀናት ተቆጠረዋል።
እንደ ተማሪ ሄመን የመሰሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ፤ በከተማው በግል ትምህርት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ጠዋት ተንስተው ወደ እውቀት ገበያ ሲያመሩ በማየት አዝነው ሲበሳጩ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ታዝቧል።
የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ መምህራም ፤ ” ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበሉ የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው ” ብለዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ለመቐለ ኤፍ ኤም ቃሉን የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፤ ” መምህራኑ ጥያቄያቸው ሳይሆን ፤ ለጥያቄያቸው መፍትሄ ብለው የወሰዱት እርምጃ ጎጂ ነው ” ብሎታል።
የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ፤ ” መምህራኑ ጥያቄ ማንሳታቸው እንደ ችግር የሚቆጥር ባይሆንም ፤ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ተማሪዎች በመቅጣት ጥያቄያቸው ለመፍታት መፈለጋቸው ግን የከፋ የስህተት መንገድ ነው ” ብለዋል።
ምሁራን ፤ ” መምህራኑ ስለ ደመወዛቸው መጠይቅ ብቻ ሳይሆን የህፃናት ተማሪ ልጆቻቸው ቀጣይ አድልም ከግምት ማስገባት ነበረባቸው ” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
በመቐለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምህሩ መምህራን ስለወሰዱት ስራ የማቆም እርምጃ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጫ አሰጣለሁ ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ተከታትሎ ያቀርባል።
ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም ፤ ” ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን ” በማለት የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃቸው መዘገባችን ይታወሳል።
መረጃው ከመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ እና ከመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
@tikvahethiopia