========== “የሌባ አይነ-ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” ========= ዴቭ ዳዊት።

* “ስዩም መስፍን” የተባለው የጠላት-ብ.አ.ዴ.ን. ሶስተኛው ትውልድ አካል የሆነው ግለሰብ፥ የግል ጥቅሙን አስልቶ ያውም የአማራን ትግል ከውጭ-ወደ-ውስጥ በሚደረግ ደባ ለመጥለፍ ተልዕኮ ተሰጥቶት ከሀገሪቱ ከወጣ በኋላ፥ “ከዕዳ ወደ ፍዳ” የሚል ፅሁፍ አሰራጭቷል።
በፅሁፉ ማጠቃለያ ላይም እንዲህ ይላል፦ “ምንም እንኳ በግሌ በህዝብ ላይ ያደረስኩት በደል ባይኖርም፣ እንደ አንድ የመንግስት አካል ሆኘ በቆየሁባቸው ጊዜያት በህዝብ ላይ ለደረሰው ጉዳትና በደል ይቅርታ እጠይቃለሁ” ይላል።
የፅሁፉ ማጠናቀቂያ ላይ የሰነቀራት፥ “ይቅርታ” የምትለው ቃል ትርጉሟ ብዙ ነው።
1. የሞራል ተጠያቂነት እንጂ የወንጀል ተጠያቂነት የለብኝም ለማለት ነው።
2. በአማራ ትግል ውስጥ በደረቁ ዘው ብሎ ከገባ፥ ሊነሳበት የሚችል ተቃውሞ ካለ፥ ከወዲሁ “ይቅርታ እኮ ጠይቋል” እየተባለ green light በቀላሉ ለማግኘት ነው።
* አሰማኸኝ አስረስ የሚባል ወንጀለኛ ብአዴናዊ ባንዳን በአደባባይ እያወገዙ፥ በተመሣሣይ ወንጀል ሊጠየቅ የሚገባውን ስዩም መስፍን የተባለን መሰሪ ወንጀለኛ ባንዳ እንደ አርበኛ ለመቁጠር መንደፋደፍ፥ double standard ነው
* ሲቀጥል፥ ላለፉት አምስት አመታት የአማራ ህዝብ የነበረበት ሁኔታ፥ Conscience Shocking የሚባልበት ሁኔታ ሲሆን፥ ዋና ዋና የሚባሉ ወንጀሎች የተፈፀሙትም የዛሬ ሁለትና ሶስት ዓመት ነው።በእነዚያ ዓመታት ውስጥ፥ ይህ ባንዳ እጁን እያወጣ ውሳኔ ሲወስንና ሲያስወስን፣ የግል ጥቅሙን ሲያሳድድ፣ በዲዛይነር የተሰፋ ልብስ ለመሸመት በዱባይና ሚላን፣ በፓሪስና ማርሴይ ሲመላለስ የነበረ ወንጀለኛ ነው።
ከዚህ ወንጀለኛ ባንዳ ፅሁፍ እንደተረዳነው፥ ራሱን ከወንጀል ክስ ለመከላከል፦ The Defense of Ignorance እና The Defense of Lack of Control over the Situations/Subordinates ካርዶችን ለመምዘዝ እየተንደፋደፈ መሆኑ ነው። እንደዚህ አይነት ጊዜ ያለፈባቸውን የማታለያ ዘዴዎች በመጠቀም በአማራ ህዝብ ላይ ከፈፀምኸውና ካስፈፀምኸው ደረቅ ወንጀል ነፃ ልትሆን አትችልም
* ሲቀጥል፥ እውን ለአማራ ህዝብ የሚቆረቆር ቢሆን ኖሮ፥ ኩብለላውን ወደ ተሻለ ምቾት ወዳለባት አሜሪካ ሳይሆን፥ ጀግኖቹ ፋኖዎች ወዳሉበት ዱርና በረሃ ነበር የሚያደርገው
* አባቶቹ የሁለተኛው ትውልድ ብአዴናዊያን፥ በቢሯቸው ላይ የወያኔን አልሞ ተኳሽ አስፍረው የአማራን ወጣት በጠራራ ፀሐይ ካስጨፈጨፉ በኋላ፥ በ2018 ዓ.ም ቆዳቸውን ገልብጠው፥ “የትግሉ ባለቤቶች እኮ እኛ ነበርን፤ የውስጥ ትግል ስናደርግ ነው የነበረው” ከማለት አልፈው “እኛ በ27 ዓመቱ የወያኔ ዘመን ምን እናውቅ ነበር? ተላላኪዎች ነበርን እኮ” ሲሉ፥ ተላላው ህዝባችንም ነውርና ሴራቸውን እንደበጎ ነገር ቆጥሩ ዳግም በጫንቃው አዘላቸው። ውሎ ሳያድር፥ ትናንት በሰንሰለት ሲያስገርፉት የነበረውን ህዝብ ላለፉት ዓመታት ደግሞ በጊንጥ ሲያስገርፉት ኖሩ። በመጨረሻም የኦሮሙማው መንግስት ግፍና በደል የእያንዳንዱን አማራዊ ኑሮና ቤት ማንኳኳት ሲጀምር፥ የአማራ ወጣት “በቃኝ” ብሎ ለትጥቅ ትግል፣ ጥሎ ለመሞት ቆርጦ ተነሳ። ይህ በሆነበት ሁኔታ ነው እንግዲህ ሶስተኛው-ትውልድ የጠላት-ብአዴን ቡድን፥ ተልዕኮ እየተሰጠው “በግሌ ወንጀል ባልሰራም በአማራ ህዝብ ላይ ለደረሰው ነገር ይቅርታ እጠይቃለሁ” የምትል መሸንገያ እየተናገረ “ኮበለልሁ” የሚለው።
እነዚህ ወንጀለኛ ብአዴኖችን ከአማራ ትግል ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም አማራዊ የማህበራዊ ኑሮ ማግለል፣ ከድል በኋላም ለፍርድ ማቅረብ ያስፈልጋል ከዚያ በዘለለ፥ እነዚህ ሆዳቸው አምላካቸው፣ ምቾት አሳዳጅ፣ ባንዳና ወንጀለኛ ተላላኪዎችን እንደ ጀግና ለመቁጠርና ወደ አማራ ህዝብ ትግል ለማስጠጋት በጥቂት የብአዴን ህቡዕ አባላት የሚደረገውን ሰሞንኛ ሙከራ ፊትለፊት ተጋፍጠን ማምከን አለብን
ዴቭ ዳዊት።
