December 27, 2023 

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከሰሞኑ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የፈቀዱት ቡራኬ ላይ ማብራሪያ ሰጠ።

ከሰሞኑ የሮማዉ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ቤተክርስቲያኗ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ቡራኬ እንዲሰጡ ፈቃድ መስጠታቸዉን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ መግለጫ አዉጥቷል።

ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጋር የሚጻረር ወይንም ዉዥንብርን ሊፈጥር የሚችል ስርዓተ አምልኮን ያወግዛል ብሏል።

ሆኖም የጳጳሱ መልዕክት በተቃራኒው ተወስዷል የሚል ሃሳብ ያለዉን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጋብቻን ግን ጳጳሱ ፈቃድ አልሰጡም ብሏል።

አክሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስቀመጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም ፤ አታጸድቅምም ማለቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከመግለጫው ተመልክቷል።

ቤተክርስቲያኒቱ ሀጢያትን አትባርክም ታወግዛለች እንጂ ያለዉ መግለጫዉ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የኢትዮጵያ ባህል እና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረዉም በመግለጫው አስታዉቋል።