December 28, 2023 – Konjit Sitotaw 

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የደጋፊዎች ሥርዓት አልበኝነትን ኮነነ፤ በማህበሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን እና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጓዝኩባቸው ርቀቶች ውጤት አላመጡም እናም በእግር ኳስ መጫወቻ ስታዲየሞች የሚደረጉ ስርአት አልበኝነቶች ከአቅሜ በላይ ስለሆኑ የጸጥታ ክፍሉ ለሚወስዳቸው ማናቸውም እርምጃዎች ተባባሪ ነኝ አለ።

ይህ ጥረቴም የራሳቸውን ፍላጎት ብቻ ለመጫንና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን በሚሉ ግለሰቦች እየታወኩ ነው ያለው መግለጫ

በማህበራዊ ሚዲያ የግለሰብ ስሞችን እየጠቀሱ አሉታዊ ቅስቀሳ የሚያደርጉትና ክለቡን ለማፍረስ የሚሰሩትን ግለሰቦችና ቡድኖች የሚመለከታቸው የመንግስት አካል አደብ ያስገዛልኝም ብሏል።