
ስልሳ አመትን ያስቆጠረው በመሃል አራዳ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በአዳነች አቤቤ ትዕዛዝ መፍረሱ ተሰምቷል።
ይህ ሕንፃ የኢትዮጵያ ምዕመናን መታሰቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም በሚል በ1956 የተቋቁቅመውና በ1959 ሕንፃውን እንደገዛው በሕንፃው ላይ የተቀመጠው የእምነበረድ ማስታወሻ ያሳያል።
ቢሆንም ቅርስ ማጥፋት ልምዱ የሆነው የኦሕዴድ ስርዐት ይህንን ሕንፃ አፍርሶታል።
እዛው አከባቢ ከ40 አመት በላይ የሆነው የቴሌ ሕንፃ የፈረሰ ሲሆን የአራዳ ሕንፃም ግማሹ ፈርሶ ግማሹ ከለሩ እንዲቀየር በማድረግ ፒያሳ ቅርሶቿን እንድታጣ እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።
