
29 ታህሳስ 2023, 12:08 EAT
የሩሲያ ጦር በመላው ዩክሬን ከፍተኛ እና የተቀናጀ የተባለ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶችን ከፈተ።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ እስካሁን ድረስ 110 ሚሳኤሎች ወደ ዩክሬን ተተኩሰዋል ብለዋል።
የዩክሬን አየር ኃይል ደግሞ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ጥቃቶች በተቀናጀ ሁኔታ በተመሳሳይ ሰዓት ሲፈጸሙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ብሏለ።
ዜሌንስኪ ዛሬ የተጀመረውን ጥቃት ሲገልጹ “ሩሲያ ያላትን ጦር መሳሪያ ሁሉ ተጠቅማ” የዩክሬን ከተሞችን እየደበደበች ነው ብለዋል።
በእነዚህ ጥቃቶች እስካሁን ቢያንስ 12 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው እና ከ75 በላይ መቁሰላቸው የተገለጸ ሲሆን ባለስልጣናት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የዩክሬን ባለስልጣናት እስካሁን ድረስ የሩሲያ ጥቃት ዒላማ ተደርገዋል ከሏቸው መካከል ትምህርት ቤቶች፣ የእናቶች ሆስፒታል፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና ሕንጻዎች ይገኙበታል።
ጥቃቱን በተመለተ እስካሁን ከሩሲያ ወገን የተባለ ነገር የለም።
- አማራ ክልል፡ጥሰቶችን ያዳፈነው እና የበርካቶችን የእንጀራ ገመድ የበጠሰው የኢንተርኔት መቋረጥ29 ታህሳስ 2023
- ትራምፕ በተጨማሪ የአሜሪካ ግዛ በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይሳተፉ ታገዱ29 ታህሳስ 2023
- ቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላን ላይ ሊላላ ስለሚችል ብሎን ማሳሰቢያ ሰጠ29 ታህሳስ 2023
ሩሲያ በዚህ ታይቶ በማይታቅ ደረጃ ከፍተዋላች በተባለው ጥቃት በአራቱም አቅጣጫ የሚገኙ የዩክሬን ከተሞችን እየደበደበች ነው።
ጥቃት ከተፈጸመባቸው ከተሞች መካከል በሰሜን ዩክሬን የምትገኘው መዲናዋ ኪዬቭ፣ በደቡብ ዩክሬን የምትገኘው የወደብ ከተማ የሆንችው ኦዴሳ፣ በምዕራብ ዩክሬን ለፖላንድ ቅርብ የሆነችው ላቪቭ እንዲሁም በምስራቅ አቅጣጫ ያምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ይገኙበታል።
ሩሲያ ዛሬ አርብ በዩክሬን ሰዓታት አቆጣጠር ንጋት ላይ በከፍተችው ጥቃት ከዒላማቸው ጋር እየተላተሙ ጉዳት የሚያደርሱት ኢራን ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑ ተገልጿል።
ቭላድሚር ፑቲን ይህን የተቀናጀ ጥቃት የከፈቱት አሜሪካ ለዩክሬን የ250 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ከሰጠች በኋላ ነው።