December 29, 2023 – Konjit Sitotaw
እኛ ካላደረግነው እኛ ካላዘጋጀነው አይቻልም የሚለው የአዳነች አቤቤ አስተዳደር የጃን ሜዳውን ተዋሕዶ ኤክስፖን ማደናቀፉ እያነጋገረ ነው፤ እነ አዳነች ስም ቀይረው ሊያዘጋጁት አቅደዋል። ከአዘጋጆቹ የተሰጠውን መግለጫ ከዚህ በታች ይመልከቱት ።
በቦታው ላይ ለተከታታይ 4 ቀናት አጥር ሲታጠርና ድንኳን ሲተከል ምንም ጥያቄ ሳይቀርብ ብዙ ድካም ከተደከመና ከፍተኛ ወጪ ከወጣ በኃላ የመክፈቻ ሰዓት ሲደርስ ድንኳን ማስፈረስ እና ለኪሳራ መዳረግ ማንንም ይጠቅማል የሚል እምነት የለንም፣ የማይፈቀድም ከሆነ ቀድሞ ያልተፈቀደበትን ምክንያት ማሳወቅ እየተቻለ እና ድካምም ሳይደከም ወጪም ሳይወጣ ማስቀረት እየተቻለ በመጨረሻው ሰዓት እርምጃ መወሰዱ ፍትሐዊነት የጎደለውና ያሳዘነን እና የሚያስተባብሩ ወጣቶችንም ስሜታዊ የሚያደርግና ላላስፈላጊ ግጭት የሚዳርግ ቢሆንም በትዕግስት አሳልፈናል፣
በጃን ሜዳ የተዘጋጀው የገና 2016 ተዋሕዶ ኤክስፖን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
በጃን ሜዳ ከታኅሣሥ 11-27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የገና ተዋሕዶ ኤክስፖ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን እና ታኅሣሥ 11 ቀን 2016 የመክፈቻ መርሐ ግብር እንደሚኖር በታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የተለያዩ የሚዲያ ጣቢያዎች /መገናኛ ብዙኃን በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ መግለጫ መስጠታችን ይታወቃል፡፡
ይህ የገና ተዋሕዶ ኤክስፖ በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለና አብሮ ሠርቶ አብሮ የማደግን መርሕ ይዞ ከቦታው ስፋት አንጻር እስከ 1000 የሚደርሱ ምርት አቅራቢዎችን ለማሳተፍ በሚከተሉት አዘጋጆች የተዘጋጀ ኤክስፖ ነው 1-
1. ማርኮናል ኢንተርቴንመንት እና ኤቨንት ኃ/የተ/የግል/ማኅ
2. ጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ኤማ እና
3. ወጣቶች እና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት
4. ከኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር በጋራ በመተባበር
ይህ የተዋሕዶ ኤክስፖ ፕሮጀክት አካል የሆነው እና የመጀመሪያው የገና ተዋሕዶ ኤክስፖ ከሌሎች ኤክስፖዎች በዋናነት በሚከተሉት ይዘቶች ይለያል፡-
ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በአጋርነት በመጣመር በግብርና ምርት ላይ የተሰማሩ አርብቶ አደር እና አርሶ አደር የሆኑ ከ25 ያላነሱ አነስተኛ ነጋዴዎች በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የሚገቡበትን አሠራር መዘጋጀቱ፣
● ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በአጋርነት በመጣመር በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ከ25 ያላነሱ ኢንተርፕራይዞችን በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የሚገቡበት ምርታቸውን ለገበያ የሚያቀርቡበት ሁኔታ መመቻቸቱ ፣
● የገበያ ተደራሽነታቸው አነስተኛ የሆኑ ገዳማትና አድባራት ምርቶቻቸውን የሚሽጡበት ሁኔታ የተመቻቸላቸው መሆኑ፣
● ሌሎች ነጋዴዎችም ከሌሎች ኤክስፖ ቦታዎች አንጻር በጣም በአነስተኛ ዋጋ ገብተው ምርቶቻቸውን በቅናሽ ዋጋ እንዲያቀርቡ በማድረግ ረገድ ሰፊ ሥራ የተሠራ መሆኑ፣
● ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ለበዓል የሚሆኑ ግብአቶችን በቅናሽ ዋጋ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የነዋሪዎች የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነሱ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ መወጣትን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን
● ከዚህም በተጨማሪ በማታው ክፍለ ጊዜ በሌሎች ኤክስፖ ላይ ከተለመደው ጭፈራና የመዝናኛ መርሐ ግብር ይልቅ የሥነ ልቦና ሥልጠናዎችን በሚመጥን መልኩ ማቅረብን ጨምሮ በዓሉ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ምስጋና ላይ እና ሰውና እግዚአብሔርን ማገናኘት ላይ ያተኮረ በዝግጅት ክፍሉ ኃላፊነት በመቆጣጠር መዝሙርን እና ቃለ እግዚአብሔርን ለምዕመናን ይዞ የቀረበ ኤክስፖ መሆኑ ከሌሎች ኤክስፖዎች ይለየዋል፡፡
ይህንን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ኤክስፖ ለማድረግ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን በተለመከተ፡-
ይህ የገና የተዋሕዶ ኤክስፖ ይዞት ከተነሣ ሀገራዊ፣ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ዓላማ አንፃር ለሀገራችን የመጀመሪያ ልምድ በመሆኑ የተለያዩ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ የአካሔድ ሒደቶች ለማስተካከል የሚረዱ ሐሳቦችን እንደ ግብአት ለመውሰድ በማሰብ በኅዳር 4 ቀን 2016ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት : ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ሌሎች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ላልናቸው አካላት ጥሪ አድርገን ነበር፡፡ ነገር ግን ከተጠቀሱት የመንግሥት ተቋማት አንድም ተወካይ ባይገኝም ጥሪውን አክብረው ከተገኙት ባለሙያዎች እና ተጋባዦች ገንቢ አስተያየት ለመሰብሰብ
1. የፈቃድ ሒደትን በተመለከተ
ሀ. ከጠቅላይ ቤተክህነት ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የተዋሕዶ ኤክስፖ ፕሮጀክት እውቅና መስጠትን ተያይዞ ደብዳቤ ተጽፏል፡፡
ለ. ከጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርት እና ሥልጠና ማእከል የቦታ ኪራይ ውል በመዋዋል ፈቃድ እንዲሰጥ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ደብዳቤ ተጽፏል፡፡
ሐ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ካቢኔ ጉዳዮች ክፍል ኃላፊ ማስታወቂያ ለምን ቀድሞ እንደተነገረ በአካል ማብራሪያ የተሠጠ ሲሆን ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ይቅርታችንን በተመለከተ የትብብር ደብዳቤ ተጽፎልናል፡፡
በዚህም መሠረት የጊዜው መሔድን መሠረት ያደረገ ፈጣን ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደ ዝግጅት ክፍል ለኤቨንቱ አስፈላጊ ሒደቶች ሲደረጉ
2. የቦታ ዝግጅትን በተመለከተ
● ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ለበዓል የሚሆኑ ግብአቶችን በቅናሽ ዋጋ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የነዋሪዎች የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነሱ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ መወጣትን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን
● ከዚህም በተጨማሪ በማታው ክፍለ ጊዜ በሌሎች ኤክስፖ ላይ ከተለመደው ጭፈራና የመዝናኛ መርሐ ግብር ይልቅ የሥነ ልቦና ሥልጠናዎችን በሚመጥን መልኩ ማቅረብን ጨምሮ በዓሉ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ምስጋና ላይ እና ሰውና እግዚአብሔርን ማገናኘት ላይ ያተኮረ በዝግጅት ክፍሉ ኃላፊነት በመቆጣጠር መዝሙርን እና ቃለ እግዚአብሔርን ለምዕመናን ይዞ የቀረበ ኤክስፖ መሆኑ ከሌሎች ኤክስፖዎች ይለየዋል፡፡
ይህንን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ኤክስፖ ለማድረግ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን በተለመከተ፡-
ይህ የገና የተዋሕዶ ኤክስፖ ይዞት ከተነሣ ሀገራዊ፣ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ዓላማ አንፃር ለሀገራችን የመጀመሪያ ልምድ በመሆኑ የተለያዩ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ የአካሔድ ሒደቶች ለማስተካከል የሚረዱ ሐሳቦችን እንደ ግብአት ለመውሰድ በማሰብ በኅዳር 4 ቀን 2016ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት : ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ሌሎች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ላልናቸው አካላት ጥሪ አድርገን ነበር፡፡ ነገር ግን ከተጠቀሱት የመንግሥት ተቋማት አንድም ተወካይ ባይገኝም ጥሪውን አክብረው ከተገኙት ባለሙያዎች እና ተጋባዦች ገንቢ አስተያየት ለመሰብሰብ
1. የፈቃድ ሒደትን በተመለከተ
ሀ. ከጠቅላይ ቤተክህነት ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የተዋሕዶ ኤክስፖ ፕሮጀክት እውቅና መስጠትን ተያይዞ ደብዳቤ ተጽፏል፡፡
ለ. ከጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርት እና ሥልጠና ማእከል የቦታ ኪራይ ውል በመዋዋል ፈቃድ እንዲሰጥ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ደብዳቤ ተጽፏል፡፡ ሐ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ካቢኔ ጉዳዮች ክፍል ኃላፊ ማስታወቂያ ለምን ቀድሞ እንደተነገረ በአካል ማብራሪያ የተሠጠ ሲሆን ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ይቅርታችንን በተመለከተ የትብብር ደብዳቤ ተጽፎልናል፡፡ በዚህም መሠረት የጊዜው መሔድን መሠረት ያደረገ ፈጣን ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደ ዝግጅት ክፍል ለኤቨንቱ አስፈላጊ ሒደቶች ሲደረጉ ::
2. የቦታ ዝግጅትን በተመለከተ
ድካም የተደከመበትና ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ድንኳንና መድረክ የፈረሰ፤ የመክፈቻ መርሐ ግብሩ የቀረ፣ ተሳታፊዎችንና ስፖንሰሮችም እቃቸውን ጭነው ለመውጣት ተገደዋል፡፡
በተሠጠን ቀጠሮ መሠረት ታኅሣሥ 15 ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በቀጠሮ ቦታ ብንገኝም አሁንም ገና እንዳላለቀ እና ለከሰዓት በኃላ እንድንመለስ በተቀጠረው መሠረት ድጋሚ ብንሔድም እንደውላለን ከሚል ያልተጨበጠ ምላሽ ውጪ ምንም ዓይነት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡
ታኅሣሥ 11 ለሚጀመር ኤክስፖ እስከ ታኅሣሥ 16 ድረስ ምላሽ እና እንደዜጋ የጠየቅነው ጥያቄ በዕለቱ ባለመሰጠቱ እንደ ዝግጅት ክፍል ከነጋዴው ከኅብረተሰቡ እና ከሚዲያዎች ለሚቀርቡልን ጥያቄዎች ተጨባጭ መልስ ለመስጠት እጅግ የተቸገርን በመሆኑ ይህንን ሁኔታ ለመላው ኅብረተሰብ እና የሚዲያ አካላት ለማሳወቅ ተገደናል፡፡
ይህ ኤክስፖ በእቅዱ መሠረት ባለመከናወኑ የደረሰው ኪሳራ
● ምርቶቸን ከግለሰብና ከተቋም በመበደር ከውጭ እና ከሀገር ውስጥ የተለያዩ ምርቶችን የገዙ እና ምግብን በመሸጥ የዕለት ገቢያቸው ለማሻሻል የመጡ ነጋዴዎች የሠሩት ምግቦች ለኪሳራ ተዳርገዋል በተጨማሪም ሁሉም ነጋዴዎች ለከፍተኛ ኪሳራ እና እንግልት ተዳርገዋል፣
● ከ216 በላይ ለሚበልጡ አዲስ እና ወጣት ለሆኑ ዜጎች የሥራ እድልን መፍጠር ችሎ የነበር ቢሆንም ሳይሳካ መክኗል፤
● ለመንግሥት ከነጋዴ እና ከመግቢያ ትኬት ዋጋ ላይ ተሰብሳቢ የሚሆን ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የግብር ገቢ እንዳያገኝ ሆኗል፤
● በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሥር የሚገኘው የጃን ሜዳ ስፖርት ፣ ትምህርት ስልጠና ማእከል ገቢ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የቦታ ኪራይ እንዳያገኝ USA
● ሰርተው ለመለወጥ በባንክ ብድር ሥራውን የጀመሩት የዝግጅት ክፍሎቹ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገዋል፤
● ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አዲስ የገበያ ትስስር እና ለማህበረሰብ የዕለት የኑሮ ጥያቄ መልስ መስጠት የሚችል ፕሮጀክት የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በመሆኑም፡-
● ይህን ኤክስፖ ለማዘጋጀት ባለው አሠራር መሠረት ሁሉም ኤክስፖ አዘጋጅ ድርጅቶች የተከተሉትን የአሠራር ሂደት ተከትለን በወቅቱ ጥያቄ ያቀረብን
የፈቃድ ሰጪው አካል ባለው መመሪያ መሠረት እንዲሁም ከዚህ በፊት በነበረው ልምድም ሆነ በዚህ ዓመትም በነበረው ሁኔታ ለሁሉም ኤክስፖ ፈቃድ የሚሠጠው የሀገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በማየት በመጨረሻዎች ቀናት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ለሥራዎቻችን የሚረዱን ዝግጅቶችን ቀደም ሲል የተደረጉ ሲሆን ከእነዚህም ፡-
ሀ. ኤክስፖ የሚደረግበት ቦታን ክፍያ በመክፈል ከቦታው አስተዳደር በመረከብ
የማጽዳትና የማዘጋጀት ሥራን በማጠናቅቅ ለደህንነት ሲባል ዙሪያው እንዲታጠር ተደርጓል፡፡
ለ. ከታኅሣሥ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተሳታፊዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ድንኳን ተከላ ተከናውኗል፡፡
ሐ. የመድረክና የሳውንድ ሲስተም ተተክሏል፡፡
መ. የስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች ድንኳን፣ ማስታወቂያ እና ምርቶች እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
ሠ. ነጋዴዎች ከታኅሣሥ 11ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ጀምረው ምርቶቻቸውን ይዘው ወደ ጃን ሜዳ ማስገባት ጀምረው ነበር:
ረ. የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችም በነጻ በተመቻቸላቸው ቦታዎች ላይ ድንኳን እንዲተክሉ ተደርጓል፡፡
3. የመርሐ ግብር ዝግጅት
በማታው ክፍለ ጊዜ የሚኖሩ ትምህርቶችና መዝሙሮች በዓሉ ላይ ብቻ ያተኮረ እንዲሆን በጥንቃቄ በመሥራት ዝግጅቱ ተጠናቆ የመክፈቻው መርሐ ግብር እየተጠበቀ ነበር፡፡
በአጠቃላይ የኤክስፖውን የጉባኤውን ይዘት ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ዝግጅት የተጠናቀቀ በመሆኑ እና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ፈቃድ ለመስጠት የሠጠው ቀጠሮ ታኅሣሥ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት በመሆኑ የመክፈቻው መርሐ ግብር ከቀኑ 8:00 እንዲሆን ዝግጅት እየተደረገ ሳለ ያልታሰበ ክስተት ተፈጠረ፡፡
ይህም፡- ፈቃድ ስለ ሌላችሁ ድንኳን አፍርሳችሁ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚል ትዕዛዝ የተላለፈ በመሆኑ ለሚመለከታቸው አካላት ብናሳውቅም ምላሽ ባለማግኘታችን አስገዳጅ በሆነ መንገድ የተተከሉ ድንኳኖችን እና ለመርሐ ግብር የተዘጋጁ የመድረክ እና ሳውንድ ሲስተሞችን አፍርሰን እንድንወጣ ተገደናል
በዛው ዕለት ጠዋት ከፈቃድ ሰጪው ቢሮ የማታ ጉባኤውን ትተናል ብላቹህ ደብዳቤ አስገቡ በተባለው መሠረት ታኅሣሥ 11 ቀን 2016 ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በቢሮ የተገኘን ቢሆንም ተነጋግረን ውሳኔ የምንሰጣችሁ ለሰኞ ታኅሣሥ 15 ቀን 2016 ቀን ነው በማለታቸው ከፍተኛ
ቢሆንም እኛ በማናውቀው ምክንያት ምንም ምላሽ ሊሰጠን ባለመቻሉ እና የተተከለው ድንኳን እንዲፈርስ በመደረጉ ኤክስፖው በተፈለገው ልክ እንዳንሠራ በመደረጋችን በጣም ማዘናችን ለመግለጽ እንወዳለን፣
● በተጨማሪም በቦታው ላይ ለተከታታይ 4 ቀናት አጥር ሲታጠርና ድንኳን ሲተከል ምንም ጥያቄ ሳይቀርብ ብዙ ድካም ከተደከመና ከፍተኛ ወጪ ከወጣ በኃላ የመክፈቻ ሰዓት ሲደርስ ድንኳን ማስፈረስ እና ለኪሳራ መዳረግ ማንንም ይጠቅማል የሚል እምነት የለንም፣
● የማይፈቀድም ከሆነ ቀድሞ ያልተፈቀደበትን ምክንያት ማሳወቅ እየተቻለ እና ድካምም ሳይደከም ወጪም ሳይወጣ ማስቀረት እየተቻለ በመጨረሻው ሰዓት እርምጃ መወሰዱ ፍትሐዊነት የጎደለውና ያሳዘነን እና የሚያስተባብሩ ወጣቶችንም ስሜታዊ የሚያደርግና ላላስፈላጊ ግጭት የሚዳርግ ቢሆንም በትዕግስት አሳልፈናል፣
● በሁኔታው ኪሳራ የደረሰባችሁ ደንበኞቻችን፣ የአገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች አስተባባሪዎች እና መርሐ ግብራችሁን በአግባቡ ለኤክስፖ ባህሪና ፍላጎት ልክ ለተዘጋጃችሁ አጋሮቻችን በየቀኑ በቦታው ላይ ከክፍለ ሀገር እና ከሩቅ መኖሪያ መንደሮች በመምጣት ኤክስፖን ለመጎብኘት ትኬት ለመግዛት የደከማቹህ እና እንዲሁም በተለያየ መልኩ የተጎዳችሁ በሙሉ በተፈጠረው ነገር በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እንጠይቃለን፣
● በቀጣይ በዚህ ጉዳይ የተለየ ነገር ካለ የምናሳውቅ መሆኑንም ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
እግዚአብሔር ሀገራችንና ሕዝባችን በሰላም ይጠብቅልን!