የማለዳ ወግ …
” እባካችሁ ልጆቻችን ተውልን “
=====================
* ልጆቻችን ነጭ አምላኪ ሳይሆን ፈጣሪን ፈርተው እንዲያድጉ ፍቀዱልን
የትምህርት ሚኒስትር በአቡነ ጎርጎሪዮስ ተማሪዎች በትምህርት ወቅት መንፈሳዊ መዝሙር እንዳይዘምሩ እገዳ መጣሉን ሰምተናል ። ምንም ማድረግ ባይችሉም በርካታ ወላጆች ልጆቻችን ነጭ አምላኪ ሳይሆን ፈጣሪን ፈርተው እንዲያድጉ ፍቀዱልን ” በሚል በውሳኔው ላይ ከፍ ያለ ተቃውሞ እና ቅሬታቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ይገኛሉ ።
እኔም እላለሁ…
==========
በህዝብ የመንግስት ት/ቤቶች የማለዳ ትምህርት መጀመሪያ ሰዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ውጭ በመዝሙር ወይም በጸሎት ዱአ በህብረት መዘመር አግባብ አይደለም ቢባል ልስማማ እችል ይሆናል ። ነገር ግን እንደ አዎሊያና አቡነ ጎርጎሪዎስ ባሉ የእምነት ተቋማት ስር በግል የሚተዳደሩ ት/ቤት ተማሪዎች መዝሙር አትዘምሩ ብሎ እገዳ መጣል አግባብነቱ ለእኔም አልገባኝምና እነሆ አጠይቃለሁ …
* ” የጥበብን መጀመሪያ ፈጣሪን መፍራት ነው” እናም ልጆቻችን በእምነት ተቋማት ስር በሚተዳደሩ ት/ቤቶች ልጆቻችኝ ክርትያኑም በመዝሙር ፣ ሙስሊም በዱአ ጸሎት እና ምስጋና ትምህርት የመጀመራቸው ጉዳት ምኑ ላይ ነው ![]()
* ሀገራችን በረከሰ የግብረ-ሰዶማውያን መስፋፋት እየናወጠች ዝም ተብሎ ልጆቻችን ኢትዮጵያዊነት ሥነ-ምግባር ታንጸው ፤ ፈጣን በመፍራት በግብረ – ገብነት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ፣ በእውቀት ጎልብተው ፣ ታሪክና የባህል ውርሳቸውን አክብረው ቢማሩ ምን አለበት ![]()
* ከስር መሰረቱ በግብረ- ገብነት ኮትኩቶ ልጆቻችን ማሳደግ የወላጅ ደጋፊ ፣ ሀገር ፣ ወገን አክባሪ፣ ልማትና እድገት የሚሰሩ በአዳዲስ እሳቤዎች መፍለቂያ ምንጭ እንዲሆኑ ማገዝ አይደለምን ![]()
* ታዳጊ ልጆችዎ የነገ ህልማቸውን የሚያልሙትን ምህዳርን ማስፋት ፣ በስልጡኑ አለም የተሳሳተ ስነ ልቦና ተጠልፈው ከስጋና ነፍስ ስብራት እንዳይጎዱ መታደግ አይደለምን ![]()
* ልጆቻችን በራሳቸው ማንነት እንዲኮሩ በልሳነ ግዕዝን ማስተማር ይጠቅማል ብየ አምናለሁ ። ከእምነት ውጭ እንደ ቀደምት ቋንቋ ግዕዝ እንደ ትምህርት የመማራቸው ጥቅሙ በቀደሙ አባቶቹ የተላለፉ መጻሕፍት እና ድርሳናትን ትውልዱ በራሱ መንገድ ተጉዞ አለምን እንዲመረምር እገዛ አያደርግም ትላላችሁ ![]()
እባካችሁ ልጆቻችን ነጭ አምላኪ ሳይሆን ፈጣሪን ፈርተው እንዲያድጉ ፍቀዱልን … ልጆቻችን ተውልን ![]()
ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓም
