በፈጣሪ ስም ድምፅ እንድትሆኑን እንማፀናለን። በብሔራችን ምክንያት ከስራችን ሊያፈናቅሉን እየተሯሯጡ ነው።
በአጭሩ ላስረዳ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥቅምት/28/2016 በ32 የስራ መደብ 392 ሰው አዲስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል ይህን ማስታወቂያ ያወጣው ተጨማሪ የሰው ሀይል አስፈልጎ ሳይሆን ነባሩን ሰራተኛ ለማፈናቀል ነው። (ከበቂ በላይ ሰራተኛ አለ። ለምሳሌ በኛ ቅርንጫፍ ብቻ 1 ሰው በሚያስፈልግበት የስራ መስክ ላይ 2-3 ሰው ትርፍ አለ)።
በስራ ማስታወቂያው ላይም “ከአማርኛ ቋንቋ ውጪ የምትችሉ” ይላል፤ ይሄንን ጥያቄም ያስገቡት እውነት ለህዝብ ከማሰብ አይደለም። ለሴራ ነው። ለመልካም ቢሆን ምንም አልነበረም ።
ነገር ግን በታህሳስ 12/2016 ዓ.ም “ኑ ለ3 ቀን በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና አለ” ብለው ጠርተውን “በቅርቡ ፈተና ስላለ ፣ ብትሰናበቱ እንኳ ራሳችሁን አዘጋጁ ” ብለው ቃል በቃል አስጠነቀቁን።
ከዚህ ቀደምም ከ7 ወር ገደማ ጀምረው ለሶስት ጊዜያት ያህል ብሄራችንን ጠይቀውናል። “ለምንድ ነው ደጋግማቹ ምጠይቁን?” ስንላቸው፣ “ፋይል እየጠፋብን ነው” አሉን።
እና እባካችሁ ከስራ አፈናቅለው ጎዳና ከመበተናችን በፊት ድምፅ እንድቶኑን እንማፀናቹሀለን። እባካችሁ ጉዳዩ ግዜም የሚሰጠው አይደለም።
ምንጭ = ለባልደራስ ፓርቲ የደረሰው አቤቱታ ነው