December 30, 2023 

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በቾ ወርዳ አዋሸ ቡኔ ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ከሌሊቱ 5:00 ሰዓት ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አራት ሰዎች እንደተገደሉ ታውቋል።

በጥቃቱ 28 የጭነት ተሽከርካሪዎች ተቃጥለው ከጥቅም ውጭ መሆናቸውንም ምንጮች ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ተሽከርካሪዎቹ ከወሊሶ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ መኾኑን የገለጡት ምንጮች፣ ተሽከርካሪዎቹን አስቁመው ቤንዚን አርከፍከፈው እንዳቃጠሏቸው ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ ተሽከርካሪዎችን ካቃጠሉና አራቱን ሰዎች ከገደሉ በኋላ፣ በርካታ ሰዎችን አፍነው እንደወሰዱና ሌሎች ደሞ ከአካባቢው በመሸሽ ሕይወታቸውን እንዳተረፉ ሉማወቅ ተችሏል።
ዋዜማ