December 30, 2023 – Konjit Sitotaw
የሽግግር ፍትህ የባለሙያዎች ቡድን ያረቅቀቀውን ብሄራዊ የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አቅጣጫ አማራጭ ሰነድ ትናንት ይፋ አድርጓል።
ቡድኑ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ባካሄዳቸው ተከታታይ ውይይቶች፣ ጉልህ በኾኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎች እንዲኹም ከፍተኛ ተሳትፎ ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ እንዲመሠረት ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
አብዛኞቹ ተወያዮች፣ ክሶቹ በአዲስና ልዩ ፍርድ ቤት እንዲታዩና የእውነት አፈላላጊ ተቋምም እንዲቋቋም ሃሳብ ማቅረባቸውን ቡድኑ ትናንት በሰጠው መግለጫ ገልጧል።
ረቂቅ ሰነዱ ከሦስት እስከ አራት ሳምንታት ውስጥ ለመንግሥት ውሳኔ ይቀርባል ተብሏል።