( ኢትዮ 360- ታህሳስ 20/2016) በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራና በረህት ወረዳ የገባው ገዳይ ቡድን ተኩስ መክፈቱንና ከባድ መሳሪያ ወደ ንጹሃን መኖርያ ሲያስወነጭፍ መዋሉን የፋኖ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በተለይ በምንጃር አካባቢ ከቀትር በሁዋላ በንጹሃ መኖሪያ ቤት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽም መዋሉንም ተናግረዋል።
የፋኖ ሃይልም ዙሪያ ከተማውን ከቦ የሄንን ገዳይ ቡድን በጥይት እያርገበገበው ነው ብለዋል ለኢትዮ 360 ባደረሱት መረጃ።
ይሄ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ሰአትም በፋኖ የበላይነት ጦርነቱ እንደቀጠለ መሆኑንም ገልጸዋል።
ወደ ሰሜን ሸዋዋ ደራ ገዳይ ቡድኑን ለማስገባት እየሞከረ ያለው የሰው በላ ስርአት በበረህት ወርዳ ጅራሬ አካባቢ ጦርነት መክፈቱንም ተናግረዋል።
በበረህትና ምንጃር ነንጹሃንን እየፈጀ ያለው የሰው በላ ስርአት ደምበጫን ጨምሮ በደጋ ዳሞትና ፈረስቤት የድሮን አሰሳ ሲይደርግ መዋሉንም አመልክተዋል።
