December 30, 2023

(ኢትዮ 360- ታህሳስ 20/2016)በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና ቁጥራቸው ወደ 16ሺ የሚደርሱ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የገዳዩ ቡድን ሃይል ተከበው ምዘና የሚል ስም የተሰጠውን ፈተና ሲወስዱ መዋላቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

የዛሬው ፈተና ባለፈው ከተቋረጠው የሚለየው ለፈተና የተቀመጡ ሠራተኞችን በከተማ ኦቶብሶችና ገጠር በሚሠማሩ ኦቶብሶች ጭኖ በየፈተና ጣቢያው ማምጣቱ ብቻ ነው ብለዋል።

ከዚህ ጋ ተያይዞ ደግሞ የአ/አበባ ከተማ ነዋሪዎች እሥከ ቀትር ድረሥ ከፍተኛለሆአ ለትራንሥፖርት ችግር ተጋልጠው ውለዋል ብለዋል።

ሠራተኞች ላይ የሥነ ልቦና ጫና ለመፍጠርና ለማሥፈራራትም በየመፈተኛ ጣቢያዎቹናአካባቢዎቹ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰው በላው ሃይሎችና ደንብ አሥከባሪዎችን ማሰማራታቸውን ተናግረዋል።

በተለይ ፈተናዎቹ በተሰጠባቸው ዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ መሠናዶ ት/ቤት፣ አዲሥ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲሥ አበባ የድሕረ ምረቃ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ የፖሊሥና የትራፊክ ፖሊሥ ተሰማርቶ መዋሉንም ይናገራሉ።

የየመሥርያ ቤቶች ሞተር ብሥክሌቶችም ለትራፊክ ፖሊሥ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገው ውለዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም፣ በፕላንና ልማት ኮሚሽን እና ከምኒሊክ ት/ቤት ጎን ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ቅጽር ጊቢም በርካታ የገዳዩ ቡድን ሃይል በተጠንቀቅ ቆሞ ሲጠብቅ መዋሉንም አንስተዋል።

መገናኛ የያዙ እና ያልያዙ የሥርአቱ ሠላዮችም ውርውር ሲሉ ውለዋል ብለውል የኢትዮ 360 ምንጮች።

ከብሔራዊ ሙዝየም እሥከ አንበሳ ጊቢ ያሉ መናፈሻዎችም ሰው እንዳይገባ ተደርጎ በፖሊሥ ሲጠበቁ መዋላቸውንም ተናግረዋል።

በአገሪቱ ሕግ አንድ ሠራተኛ ማሥታወቂያ አይቶ ተመዝግቦና ፈተና ተፈትኖ ካለፈ በኋላ አዲሥ ፈተና የሚባል ነገር የለም በሚል አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች አስተያየት በመስጠት ላይ መሆናቸውንም ይናገራሉ።

የሕግ ባለሙያዎቹ አክለውም እነዚህ የመሥተዳድሩ ሰራተኞች ፍተና አልፈው የ3 ወር የሙከራ ጊዜያቸውን በማጠናቀቅ በቋሚነት ከተቀጠሩና ከ5 እሥከ 15 አመት አመት በላይ ያገለገሉ ሆነው ሳለ ፈተና መባላቸው ሕግ ያለመኖሩን አመላካች ነው በሚል ትችታቸውን በመሰንዘር ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ነገር ግን ይሄ ፈተና የሰራተኛውን አቅም ለመፈተሽ ሳይሆን ዋናው አላማው በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራና የደቡብ ብሔር ተወላጆችን ከስራ ገበታ የማፈናቀል ዘመቻ መሆኑን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ በዘገባው ማውጣቱ ይታወሳል።

ከዚህ አልፎ ይላሉ ምንጮቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱ ያወጣውን መመሪያ በመጣስ መንግስት ሰራተኞች የጽሑፍ ጥያቄ ብቻ እንዲፈተኑ አድርጉቸዋል ብለዋል።

መመሪያው ምርጫ፤አዛምድ፤ዳሽ ሞላና የማብራሪያ ጽሁፍ ይላል ነገር ግን ሁሉም በራሱ ሁሳብ የሚመልሰውን ጥያቄዎችን በማዘጋጅት ውጤት ለሚፈልጉት ባለጊዜ ለመስጠት የተመቻቸ ነው ሲሉም አጋልጠዋል።

ከፈተናው በፊትም ተቋማቱን እንዲወሩ ለተመቻቹት የሰው በላው ስብስቦች መልሱ አስቀድሞ እንደተሰጣቸውም ኢትዮ 360 በመረጃው በተደጋጋሚ ማውጣቱንም አንስተዋል።

ምናልባትም አሁን ላይ እየተሰራ ካለው ብሔርን ለይቶ የማጥቃት ዘመቻ ጋር ተያይዞ በቅርቦ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራና የደቡብ ተወላጆች ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለው ከነቤተሰቦቻቸው ሜዳ ላይ የሚበተኑ ይሆናል የሚለውንም ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ ሲያጋልጥ መቆየቱን አንስተዋል።