December 30, 2023 

(ኢትዮ 360 – ታህሳስ 20/2016)በአዲስ አበባ ከተማ በጥቁር ገበያ ዶላር ትመነዝራላችሁ በሚል በርካታ የንግድ መደብሮች ሲታሸጉ መዋላቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።

እየታሸጉ ያሉት ሱቆች ደግሞ ሕጋዊ ተከራይና ግብር ከፋይ የሆኑ ናቸው ብለዋል።

በዶላር እጦት የሚያደርገው የጠፋው የሰው በላው መሪ የንግድ መደብሮቹን በዋናነት ያሳሸገበት ምክንያት በቅርቡ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ የሚመጣ ውን ዶላር ይሻሙኛል በሚል ነው ይላሉ ምንጮቹ።

እንደ ምንጮቹ ከሆነ በጨርቆሥ ክፍለ ከተማ ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ንብረትነቱ የበላይነሕ ክንዴ የሆኑትን ሱቆች የተከራዩ ነጋዴዎች በክፍለ ከተማው ንግድናኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ማሕተም መታሸጋቸውን አስታውቀዋል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ኢትዮ ቴሌኮም እና ጋንዲ ሆሥፒታል አካባቢ ያሉ ሱቆችም በተመሳሳይ መልኩ መታሽጋቸውን ገልጸዋል።

ድርጊቱን ፈጻሚዎች ባልተለዩበትና የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ሊካሄድ ወራት በቀሩበት ሱቆቻችን መታሸጋቹው ከነቤተሠቦቻቸው ጦም እንዲያድሩ የማድረግ ሂደት ነው በሚል ነጋዴው ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በጥቁር ገበያ ዶላር የሚመነዝሩትን እነሱና ፖሊሶቻቸው ያውቋቸዋል ለምን ነጥለው ለሕግ አያቀርቧቸውም በሚል ጥያቄ ማቅረባቸውንም አንስተዋል።