December 31, 2023 

(ኢትዮ 360- ታህሳስ 21/2016) ከባህርዳር እስከ ደንበጫ ባሉ አካባቢዎች የታፈሱና 15 ተሽከርካሪ ሙሉ ወጣቶች ወደ አልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ መሆኑን የፋኖ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።

ይሄ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ሰአትም ወጣቶቹን የጫኑት ተሽከርካሪዎች አማኑኤል አካባቢን እያለፉ መሆኑን ይናገራሉ።

በተሸከርካሪዎቹ ውስጥ ከተጫኑት አብዛኞቹ ህጻናት ሲሆኑ አልፎ አልፎ አዛውንቶች እንደሚገኙበትም አስታውቀዋል።

ከታፈኑት መካከልም ምንም ልብስ ያለበሱና ራቁታቸውን ያሉ ህጻናት መኖራቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

ተሽከርካሪዎቹ በዚህ ሰአት ወደ ደብረማርቆስ እያመሩ ቢሆንም መጨረሻቸው ግን የት እንደሚሆን አልታወቀም ብለዋል።

በአካባቢው ያለው የፋኖ ሃይል ጥቃት ፈጽሞ እነዚን ወጣቶች ማስፈታት እንዳይችል ደግሞ ወጣቶቹ ላይ ጉዳት ያደርሱባቸዋል በሚል በቅርብ እርቀት ነገሩን እየተከታተሉት መሆናቸውንም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።