December 31, 2023 – Konjit Sitotaw
(ኢትዮ 360- ታህሳስ 21/2016) ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ባህርዳር ለመግባት የሞከሩ ነዋሪዎች ኬላ ላይ መታወቂያቸው እየታየ እየታፈኑ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ኢትዮ 360 በአርብ ዕለት ዘገባው የባህርዳር ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ ያልያዘ የክልሉ ነዋሪ ወደ ባህርዳር እንዳይገባ መመሪያ መውረዱን ማጋለጡን ያስታውሳሉ።
ይሄንን መመሪያ እንዲወርድለት የተደረገው የባንዳና የሰው በላ ስብስብ ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጡ ነዋሪዎችን መታወቂያቸውን በማየት ወደ ከተማዋ እንዳያልፉ በማድረግ ላይ ነው ብለዋል።
በተለይ ደግሞ ወደ ከተማዋ ለመግባት የመጣው ወጣት ከሆነ ያለምንም ጥያቄ ወደ ማጎሪያ ይጋዛል ብለዋል።
በሰው በላው ስርአት አዲስ አበባ መግባት አትችልም የተባለው የአማራ ተወላጅ አሁን ደግሞ ወደ ባርዳር ከተማ አትገባም በሚል በጅምላ እየታፈነ ነው ብለዋል የኢትዮ 360 ምንጮች።