January 1, 2024 – Konjit Sitotaw
በጎጃም መስመር ያሉ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ነዋሪዎች ለሰው በላው ስርአት ግብር አንከፍልም በሚል ማመጻቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ለአካባቢው ነዋሪዎችም ሆነ ለንግዱ ማህበረሰብ አባላት በተደጋጋሚ የግብር ክፈሉ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም እስካሁንም አንከፍልም በሚል አቋማቸው ጸንተው መቆማቸውን ተናግረዋል።
ግብር ላለመከላቸው ምክንያቱ ደግሞ ገቢያቸው የነበረው በአካባቢውከሚመላለሱ መንገደኞች ነበር ያ ደግሞ አሁንየለም ስለዚህ ከየትም አምጥተን አንከፍልም በሚል መሆኑንም አመልክተዋል።
ግብር እንዲከፍሉ ከተፈለገም የዱሮውን ስራ ይመለስ ተሽከርካሪዎችም ሥራቸውን ይሥሩልን ያ ካልሆነ ግን ምንም አይነት ግብር አንከፍልም በሚል ማመጻቸውን ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ሸዋ ምንጃርና አካባቢው ፍተሻ አድርጋለሁ ብሎ የገባው ገዳይ ቡድን በፋኖ ሃይል ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል።
በገጠመው ከባድ ሽንፈት የተበሳጨው ገዳይ ቡድንም ተራራና በንጹሃን መኖሪያ ቤት ላይ ከባድ መሳሪያ ሲያስወነጭፍ መዋሉን ተናግረዋል።
ተራራዎችን በመድፍ ሲደበድብ የዋለው ገዳይ በነዋሪዎች ቤት ላይም በፈጸመው ጥቃት አንድ አርሶ አደርን ገሎ አንድ ማቁሰሉን ተናግረዋል።
ከሁለቱ ሌላ የተጎዱ ቢኖሩም ቁጥራቸውን በትክክል ማወቅ አልተቻለም የሚሉት ምንጮቹ በርካታ የቤት እንስሳት መገደላቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባት አቡነ ቶማስ ያስተላለፉት መልዕክትን ተከትሎ ከየአካባቢ የሚሊሻና የአድማ ብተና የሚባሉ ስብስቦ ለፋኖ እጅ መስጠታቸውን ተከትሎ ከባድ ድንጋጤ መፈጠሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።
ከሰሜን ሸዋ አካባቢ ብቻ በአንድ ለሊት ወደ 35 የሚደርሱ የሚሊሻ አባላት ከነመሳሪያቸው ጠፍተው ማደራቸውን ይናገራሉ።
ይሄንን ተከትሎም ለኦህዴዱ መከላከያ የተለየ ትእዛዝ እንደወረደለትም አመልክተዋል።
በትእዛዙ መሰረትም የተለየ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የሚሊሻ የአድማ ብተና ብሎም የፖሊስ ሃይል ካለ እርምጃ ውሰዱ የሚል መመሪያ እንደተሰጣቸው አጋልጠዋል።
ነገር ግን መመሪያ አይደለም ምንም ቢያወርዱ ከአባቶች ትእዛዝ አልወጣም ያለው ሃይል ከየአቅጣጫው የፋኖ ሃይልን ከነመሳሪያቸውን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል ብለዋል ምንጮቹ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ዛሬ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተጠርቶ የነበረው ስብሰባ ምንም ሰው ባለመገኘቱ ስብሰባው ሳይካሄድ መቅረቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ተማሪውን ወደ ጦርነት ለመማገድ የተያዘውን እቅድ የሰማው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በልጆቻችን ግድያ ተሳታፊ አንሆንም በሚል አንድም ሰው ሳይገኝ ቀርትዋል ብለውል።
