
ከቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በአል መልስ መንገድ ላይ የታገቱት ምዕመናን በእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር እየተጠየቀባቸው ነው።
የቁሉቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ ተጓዙች በሞት ካጣናቸው ወንድሞች በተጨማሪ ከታች ስማቸው የተጠቀሰው ወንድሞች የታገቱ አሥር ሰዎች እና ያሉበት ሁኔታ የማይታወቁ ሁለቱ ወንድሞች በጥቅሉ አሥራ ሁለት ወንድሞች ናቸው ።
ከእዚሁ ጋራ በጣም አሳዛኙ ሌላ ጉዳይ በመንገድ ላይ አንድ ህጻን ቤተሰብ የሌለው ህጻን እያለቀስ ቢያገኙትና ቢጨነቁ ጊዜ ህጻኑ ሲጠይቁ እርቦት እንደነበረ ቤተሰብ እንደሌለው ቢነገራቸው ሁሉም በማዘን ወስደን እናሳድገው በማለት ምሥጋናው በተባለው ወንድም አማካኝነት ይዘውት እየመጡ ነበር ፤ በአደጋው ሰላባ ከሆኑ መካከል ይሄ ታደጊ ውንደኛው ሲሆን ቅዳሜ ወደ መተሐራ ሄደው የጠየቁ ቤተሰቦች ህጻን መኖሩ በጸጥታ አካሉ የተገለጸላቸው ይሄው ታዳጊ ሆኗል እጅግ ያሳዝናል ።
በአጋቾች እጅ የሚገኙት እና ለቤተሰቦቻቸው ተደውሎ ለመልቀቅ ገንዘብ የተጠየቀባቸው አሥር ወንድሞ ስማቸው እነዚህ ናቸው ።
1ኛ. ማስረሻ አበበ [ ኖሻ ]
2ኛ. ጌታሁን ሁንዴቻ [ የሞች አዲሱ ሁንዴቻ ወንድም ]
3ኛ. በኃይሉ ጀምበሬ
4ኛ. አበራ ቱሉ
5ኛ. ያሬድ ታሪኩ
6ኛ. ቢኒያም ከበደ [ ነብሶ]
7ኛ.ዘሪሁን ንጉሴ
8ኛ. ያሬድ ነጋሽ [ አቢሊሉ ]
9ኛ. ቢኒያም ነጋሽ
10ኛ. ምሥጋናው
11ኛ . በኃይሉ ጆብሬ
12ኛ. አዲሱ ባይሳ
እነዚህ የተቀሩ ወንድሞች ሁሉም እንደየ እምነቱ ጸሎት በማድረግ የአጋቾችንንም ልብ አምላክ አራርቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ያሉን ሰላማዊ ጥረቶች ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል ።
ከላይ ሥማቸው የተጠቀሱት የተወሰኑት በምሥሉ የሚታዩት ናቸው !
ምንጭ ቃሊቲ ከተማ
( የኔታ ቲዩብ )