ሮጠው የታጠቁት ……. ሮጠው ተፈቶባቸው ተዋርደዋል።

የሶማሌላንድ ነገር መዘዝ ይዞባቸው ሲመጣ የመግለጫ ዝናባቸውን ማውረድ ጀምረዋል። የውጪ ጉዳዩ የመንግስት ኮሙኒኬሽኑ የጋኔን ክብሪቱ …. ሁሉም በየፊናው የአብይ አሕመድ ሰዎች የተፉትን እየላሱ አዲስ ትፋታቸውን ማቀርሸት ጀምረዋል።
አይ ሱማሌላንድ …. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንደሚባለው የወደብ ባለቤት ሆንን …. ቀይ ባሕር ላይ ተተከልን አሉን በጥሩባቸው ሳይሆኑና ሳይተከሉ ….. ቸኩለው አውርተው ቸኩለው ጨፍረው ቸኩለው ለማስቀየስ እየተሯሯጡ ነው።
ሮጠው የታጠቁት ……. ሮጠው ተፈቶባቸው ተዋርደዋል። አንድም የሚያስተውል ባለስልጣንና አማካሪዎች የሌበት አገር ጥፋትና ውሸት ብቻ መሬቱን ተቆጣጥረውታል። ….. ባለስልጣናት ኮንትሮባንዳቸውን እና የዶላርና መሳሪያ ዝውውሩን ንግዳቸውን ለማጣደፍ ሶማሌላንድን የኛ ሙሽራ ሲሏት መዘዝ ይዞባቸው መቷል።
አልሸባብ ሊናከስ ጥርሱን እየሞረደ ነው። ሶማሊያውያንም እንዲሁ ከየቦታው ተቃውሞ እያሰሙ ነው። ሃገራትም አህጉራትም የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ቀውስን እንደማይፈልጉ እየተናገሩ ነው።
ሲንቀዠቀዡ ለሃገር እዳ እያመጡ ነው። በሃገር ስም ተበድረው የዘረፉት አልበቃ ሲላቸው የስማችን መተሪያ የሆነውንም አየር መንገድ ገለው ሊቀብሩት አሰፍስፈዋል። በጣም አሳፋሪ ነው። ማስተዋል ያስፈልጋል።
የአራቱንም ማዕዘን የውስጥና የውጪ ፖለቲካ መገምገም አይችሉም ። አማካሪዎችን አቅጣጫ ጠቋሚዎችም የሉም። ለዚህ ነው በሳል መሪና በሳል ባለስልጣን ያስፈልጋል ብለን የምንጮኸው። #MinilikSalsawi
Photo credit : Amin Amir page-ka Ra’iga