January 3, 2024 – Mereja.com

ለጃርቱ ዘንዘሪጡ ዳንኤል ክብረት

ማስገንዘቢያ፣ ቀሲስ አስተ ርአየ ጽጌ አምና “ጃርት ለምን ይጮኸል” በሚል ርዕስ ፋኖን ተሳድቦ ጽፎ ጃርትም ቀበሮም አይጥም ራሱ ዘንዘሪጡ ዳንኤል እንደሆነ ለመሰሉት ሁሉ ትምህርት ሰጭ መስከረም 3 ቀን 2015 ጽፈው ቤተ ክርስቲያናችን በሚመጥን ቋንቋ ባቀረቧት ጦማር በክፈተው አፉ አስገብተውበት ነበር። ደጋፊ ሆኖ ለተሰለፈው ዶ/ር ዳኛቸውም መልሱን ሰጥተው ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በአፈ ቀላጤነቱ አባ ሉቃስን ቆብዎን ያውልቁ የሚል ቀጭን ትዛዝ አስተላልፏል። እስከ አሁን በቤተ ክርስቲያንና በአገር ላይ ማንም የወረወረውን ድንጋይ ቀልበው ወርዋሪውን መልሰው የመምታት አቅምና ብቃት  ያላቸው ቀሲስ አስተርአየ ብቻ መሆናቸው የታወቀ ነው። “ቆብዎን ያውልቁ” ብሎ  በአቡነ ሉቃስ ላይ በከፈተበት አፉ ራሱ የተናገረውን  ርዕስ አድርገው አዘጋጅተው ቢለቁበት ለሱና ለመሰለቹ  አመርቂና አስተማሪ በሆነ ነበር። እሁን ከምንገኝበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያያዥነት ስላላትና እንድትጠቀሙበት “ለጃርቱ ዘንዘሪጡ ዳንኤል ክብረት” በሚል ርዕስ የጻፏትን ጦማር በድጋሚ እቅርበንላችኋል

ለጠ/ም ዓቢይ አፈቀላጤ ዳንኤል ክብረትም ትድረስ “ጃርት ለምን ይጮኻል?” “ጃርት ለምን ይጮኻል? በሚል ርዕስ የጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይ አፈ ቀላጤ ዳንኤል ክብረት በጠልስሙ ያቀረባትን ጃርት በቤተ ክርስቲያናችን ስነ ጽሑፍ (ቅኔ) ስልት እንዳቀርባት ለጠየቃችሁን ይህችን “ልፋፍ” አቀርብኩላችሁ፡፡ ጠልሳሚው የጠ/ም ዓቢይ አፈቀላጤው ዳንኤል ክብረት “በተጠያቂ አባት፤ በጠያቂ ልጅና በሚጮኸው ጃርት” አንጻር በጠመዝማዛ ፈሊጥ እነማንን ለመግለጽ አንዳሰበ ራሱ ስላልገለጸው እርግጠኛ በመሆን መናገር አልችልም፡፡ ይሁን እንጅ በዚህ አይነት ጠመዝማዛ ፈሊጥ የሚቀርቡትን አወናባጅ ሀሳቦች እንዴት መተርጎም እንደምችል የቅኔና የአ አንድምታ ትርጓሜ መምህሮቻችን ባሳዩኝ ጥበብ ገልጨ ላቀርብላችሁ እሞክራለሁ፡፡ ማእምራን አንባቢወቼ ሆይ! አተረጓጎሜን በቀላሉ ትረዱልኝ ዘንድ፡ ወደ ትርጓሜው ከመሻገሬ በፊት ኢትዮጵያዊውን ያተርጓጎም ስልት ብገልጸው መልካም መስሎ ታየኝ፡፡

“መጀመሪያ ተናገሪው የተናገረውን ጥሬ ነገር አጥናልሁ፡፡ እንዲናገር ያስገደደው ስውር ኃይል እንዳለ እገነዘባለሁ፡፡ በመቀጠል የንግግሩን ይዘት በጥንቃቄ አስተውላለሁ፡፡ 2 ያጠናሁትን የተገነዘብኩትን ያስተዋልኩትን በጭንቅላቴ ቋጥሬ በሹክሽክታም ሆነ በይፋ በህብረተሰቡ መካከል ወደ ሚብላላው ወቅታዊ ንግግር ለመሻገር በጃርቷ እጀምራለሁ፡፡ ጃርት ከሚመስሏት ብዙ ነገሮች አንዷ አይጥ ናት፡፡ ወደ አይጥነት የተጠጋች አይጥ የመትመስል ትልቅ አይጥ ናት፡፡ አካሏ በእሾህ የተሸፈነ ነው፡፡ ፈረንጆች quill ይሉታል፡፡ የሚዋጋ የሚመስል ወግቶ የማያጠቃ አስመሳይ ጦር ለማለት ይመስለኛል፡፡ ጥቃት የምትከላከለው በጦር መሰል እሾኋ ነው፡ አጥር እየጣሰች አቅጣጫ እየቀየረች በሰው ጓሮ በመግባት ዱባውን ድንቹን ጎመኑን የምታበላሽ አስቸጋሪ አይጥ ናት፡፡ የበላቸውን በልታ አዘርክርካ የምትተወውን “ጃርት እንደበላው ዱባ የተዘረከረከ” እየተባለ ለተበላሽ ነገር እንገልጽበታለን፡፡ እሾኋን አንጨፍረራ በማቆም የሚሰነዘርባትን ዱላ ታነጥረዋለች፡፡ ራሷን በእሾኋዋና በፊት እግሮቿ የምትደብቅ ብልጣ ብልጥ ፍልፈል ናት፡፡ የምትሞተው ገና ተጫዋች ጎልማሳ በገና ጨዋታ እንደሚለጋት ጥንግ አፍንጫዋን ከተከለችበት ሳር ጋራ ከመሬት ጠርጎ ሲያጠነጋት ብቻ ነው፡፡ የገጸ ባህርዋን ትርጓሜ በኋላ ለማምጣት እዚህ ላይ ላቁምና እሷን ከሚመስሉት ወደ አንዷ ወደ ቀበሮዋ ልሻገር፡፡

ቀበሮ ቀበሮና ጃርት በአውሬነታቸውና በሚያደርሱት ጥፋት ይመሳሰላሉ ፡፡ ጃርት ከላይ እንደገለጽኩት እሾሀም ስትሆን ቀበሮ ጅራታም ናት፡፡ ጅራታማዋ ቀበሮ ከጃርቷ ይልቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተደጋግማ ባጥፊነት ተጠቅሳለች፡፡ 3 ቀበሮ የቂመኛ ተላላኪ በቀል ፈጻሚ ናት፡፡ ሶምሶን በቂም ተነሳስቶ ፍልስጤማውያንን የተበቀላቸው በቀበሮ ነው፡፡ የፍልስጤማውያንን አዝመራ እንዲያቃጥሉ እሳት የተለኮሰ ችቦ በጅራታቸው ቋጥሮ የሰደዳቸው ቀበሮወችን ነው፡፡ (መሳ 15፡4) ጠቢቡ ሰሎሞን የወይን ቦታ ተክሉን አበባውን እየገቡ የሚያጥፉ ናቸውና ያዙልን ያለው ቀበሮወችን ነው (መኃ 2፡15) ፡፡ ክርስቶስ ወደ ሕብረተ ሰቡ የገቡትን አጋንንት ማስወጣቱን አቁሞ አገሩን ለቆ እንዲሄድ ሄሮድስ ላከበት፡፡ ክርስቶስ “ዛሬና ነጋ አጋንንትን አወጣለሁ ሕመምተኞችን እፈውሳለሁ ብላችሁ ንገሩት” ብሎ ፈሪሳውያንን መልሶ ወደ ሄሮድስ ሲልካቸው የሄሮድስን ባህርይ የገለጸው በቀበሮ ነው፡፡ (ሉቃስ 13፡32)፡፡ ከጃርቷ ጋራ ባንድምታ ተጠልፋ በገባችው በቀበሮዋ ገጸ ባህርይ ወቅቱን ለመተርጎም በሕብርተ ሰቡ መካከል የሚብላሉትን ክስተቶች እንጠይቅ፡፡ 1ኛ፦እሳት የተለኮሰ ችቦ ተሸክመው አዝመራ ያቃጠሉት ቀበሮወች ዛሬ በአገራችን እነማንን ይገልጻሉ ? 2ኛ፦እሳት አሸክሞ የለካው ሰውስ ዛሬ በአገራችን ማንን ይመስላል? 3ኛ፦ጠቢቡ ሰሎሞን በወይን ቦታ እየገቡ የሚያጠፉ መያዝ የሚገባቸው ቀበሮወች ያለቸው እነ ማንን ይገልጻሉ? 4ኛ፦ ወደ ሕዝቡ መንደር የገቡት አጋንንት እነማንን የሚገልጹ ይመስላችኋል? 4 5ኝ፦የገቡትን አጋንንት ለማሰወጣት የተሰማራው ክርስቶስስ ማንን የሚገልጽ ይመስላችኋል? 6ኛ፦አጋንንት ማስወጣቱን እንዲያቆም እንቅፋት ሆኖበት ክርስቶስ ቀበሮ ያለው ሰውስ ማንን የሚገልጽ ይመስላችኋል?

ከዚህ በመቀጠል ጠልሳሚው ዳንኤል “ጃርት ለምን ይጮኻል?” በሚል ርእስ የጀመራትን ጠልሰም “እኛም እንሰራለን ጃርቶቹም ይጩሁ” በማለት ወደደምደመበት እንሻገር፡፡ በጃርቷ ገጸ ባህርይ ወቅቱን ለመተርጎም በሕብርተ ሰቡ መካከል የሚብላሉትን ክስተቶች በየአረፍተ ነገሮች ራሴ አጠቃልላቸዋለሁ፡፡ አጥር ጥሰው ወደ ክልሉ የገቡትን የካድሬወችንና የመከላክያውን ጫጫታ የሰማው ፋኖ “እኛም እንሥራለን ጃርቶቹም ይጩሁ” በማለት መፈክሩን እየተቀባበለው ነው፡፡ ዳንኤል ክብረት “ጃርቶች ከጮኹ በዚያ አካባቢ ምርት አለ ማለት ነው” ማለቱ ተወልዶ ያደገበትን አካባቢ እንዳልተረዳ የሚያሳይ ይመስላል፡፡ ቢረዳ ኖሮ ይህን አባባል ባልተጠቀመ ነበር፡፡ አማራው ፋኖ ባለበት በሚኖርበትና በደረሰበት ሁሉ ቦታ ምርት እንዳለ ዓለም የሚያውቀውን እንዴት አላወቀም? ፋኖ ነፍጥ አንስቶ “ጥራኝ ዱሩ” ብሎ ከከተማ ከምንደር ወጥቶ ወደ ጫካና በርሀ እንዲገባ የተገደደው አካባቢያቸውን ባልተረዱ ዳንኤል ክብረትን በመሳሰሉ አማካሪወችና ዓቢይን በመሳሰሉ ተመካሪወች በመገደዱ ነው፡፡ 5 ዳንኤል “ጃርት የራሱ ጉዳይ የለውም፡፡ የራሱ ሥራ የለውም” በማለት የጃርትን ባህርይ ገልጿል፡፡ ይህ ገጸ ባሕርይ ህዝቡን ለመመገብ ሌትና ቀን ከሚለፋው ከፋኖው ባሕርይ ጋራ የሚቃረን ነው፡፡ በትክክል የሚገልጸው ስምሪቱን ትቶ በመከላክያ ስም ወደ ፋኖው ክልል የተላከውን ነው፡፡ “ጃርት የሚችለው በሰው ሥራ መጮኽ ነው” እንዳለውም ዳንኤል፡ ብልጽግና መከላክያውን እንዲችል ያደረገው በማይመለከተው በፖሊስ ሥራ ገብቶ በየከተማው መጯጯህ ነው፡፡

ራሱ ዳንኤል እንዳለው ጃርት አጥር እየቀደደች በመሽሎክለክ “እሾህ መርጨትና ሰብል ማጥፋት ነው” ብሎ የገለጸው የጃርት ጠባይ የሚገልጸው የራሱን የዳንኤልን ባሕርይ ነው፡፡ ባንድ ዘመን እናት ቤተ ክርስቲያን በሚል እየጮኸ እርስ በርሳችን አደባደበን፡፡ በሌላ ወቅት የተሳሳተ ነገር ጽፎ አቡነ ማትያስን አስፍርሞ ከማኅበረ ካህናቱ ጋራ እንዲጋጩ አደረገ፡፡ በሌላ ወቅት በዚያው ጽፎ ባስፈረማቸው ጉዳይ ከአኀት አብያተ ክርስቲያናት ሊለዩን ብሎ ከአኀት አብያተ ክርስቲያናት ጋራ አጋጫቸው፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰንደቅ ጋዜጣ ባለቤት ጋራም አላተማቸው፡፡ በማህበረ ቅዱሳን ተሸፍኖ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምንም ከብዙ ሰወች ጋራ አጋጭቷቸዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ በብልጽግና ተሸፍኖ ጃዊሳ ጃርት እያለ በፋኖ ላይ ዘመተ፡፡ ዳንኤል ወቅት እያነበበና አቅጣጫ እየቀያየረ በሕብረተ ሰብ ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ሰበነክ ጃርት ነው ቢባል በሚገባ የሚገልጸው ይመስለኛል፡፡ ዳንኤልን የመሳሰሉትን ሰበነክ ጃርቶች ፋኖ እንዴት ነው መከላከል የሚችለው? 6 ጃርት በብዙ እሾህ ብትታጠርም፡ የሚሰነዘርባትን ዱላ በታጠረችበት እሾህ እያነጠረች ብትከላከልና አፍንጫዋን መሬት በረገጡት እግሮቿ መካከል ብትሸፍንም፡ አፍንጫዋን ከተከለችበት ሳር ጋራ አዳኙ ከመሬት ጠርጎ እንደሚያጠነጋት ዳንኤል ክብረትም በጎልማሳው ፋኖ መጠንጋቱ አይቀርም፡፡ በተረፈ፦ “ጃርት ለምን ይጮኻል?” በሚል ርእስ ጥሬ ንባቡን ላመነጨው ግለሰብ ለጠ/ም ዐቢይ አፈ ቀላጤ ዳንኤል ክብረትና፡ በሰፊው ለተነጋገራችሁበት ሕብረተ ሰብ (ለናነተ) በአብነቱ አንድምታ ፈሊጥ ተርጉሜ በማቅረብ ድርሻየን ስወጣ መምህሮቸ ያሸከሙኝ ሸክም ከትክሻዬ ሲውርድ የተሰማኝን ስሜት ከመቃተት በቀር የምገልጽበት ቃል የለኝም፡፡ ይቆየን።

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ nigatuasteraye@gmail.com