January 4, 2024 – Konjit Sitotaw
በብሄር ስብጥር ስም ሰራተኞችን ከስራ እያባረረ ያለው የንግድ ባንክ ኮሜርሻል ኖሚኒስት ከኦሮሚያ ክልል የተላኩለትን እየቀጠረ ነው።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሜርሻል ኖሚኒስት የደረሱን መረጃዎች እንዳመለከቱት በድርጅቱ ውስጥ ለረዥም አመታት የሰሩ ሰራተኞች ከስራቸው እየተባረሩ በምትኩ ከኦሮሚያ ክልል የተላኩ አዳዲስ ሰራተኞች እየተቀተሩ መሆኑን እና ይህም በንግድ ባንኩ ፕሬዝዳንት ትዕዛዝ የተፈጸመ እንደሆነ እንዲሁም ይህን የሰራተኛ መባረር አስመልክቶ የሰራተኛ ማሕበሩ ተቃውሞ እያሰማ ቢሆንም ሰሚ ማጣቱን እና ጭራሽ በቀሪው ሰራተኞችና በማሕበሩ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰ እንደሆነ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል።
የንግድ ባንኩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት በባንኩ ውስጥ እና በሰራተኞች ቅጥር በሚያከናውነው ኮሜርሻል ኖሚኒስት በተሰኘው ድርጅት በኩል የሰራተኞች የብሄር ማንነት እየተተየቀ ሲሆን ንግድ ባንክ ኦንላየን በሚያወታው የስራ ማስታወቂያ ላይ ብሄር የሚል በፎርሙ ላይ በማስፈር ተቃውሞ ያስተናገደ ቢሆንም ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በርካታ የአንድ ብሄር ተወላጆች በባንኩ ውስጥ መቀጠራቸው አሁንም ጥያቄ ማስነሳት መቀጠሉን ገልጸው ወደ ታች በመውረድም በኮሜርሻል ኖሚኒስት ነባርና የቆዩ ሰራተኞችን በማባረር አዳዲስ የአንድ ብሄር ሰዎችን መቅጠር እያወዛገበ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የኮሜርሻል ኖሚኒስት ሰራተኞች መባረርን በተመለከተ የሰራተኛ ማሕበሩ በንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ደብዳቤ ቢፅፍም የንግድ ባንኩ ፕሬዝዳንት ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ ስለሆነ ለማናገር ፈቃደና አለመሆናቸውን ቢናገሩም የሰራተኛ ማሕበሩ ጫና ማድረግ መቀጠሉ ታውቋል። የሰራተና ማሕበሩ ለንግድ ባንኩ ፕሬዝዳንት በጻፈው ደብዳቤ በሠራተኛ ቅነሳ ላይ ውይይት እና ጠቃሚ ምክክር ለማድረግ መጠየቅን ይመለከታል ይላል። በደብዳቤው ባንካችን የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አሰሪያችን የሆነው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ጋር በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ በጋራ እየሠራ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም ባንካችን በአሁኑ ጊዜ የአለውን የኑሮ ውድነት እና ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ ባላካተተ መልኩ በሀገር ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ የሠራተኞች ቅነሳ እያደረገ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳንድ ሁኔታዎች ስለአሉ ችግሩ ጎልቶ ወጥቶ የባንካችን ገጽታ ከማበላሸቱ በፊት በእርስዎ በኩል ትኩረት ተሰጥቶት በውይይት እና በምክክር ለመፍታት አስቸካይ ቀጠሮ እንዲያዘልን ስንል የኮሜርሻል ኖሚኒስ መሰረታዊ የሠራተኛ ማህበር በአጠቃላይ በኮሜርሻል ኖሚኒስ በኩል ተቀጥረው የሚሰሩትን ሠራተኞች በሙለ በመወከል በታላቅ አክብሮት በትህትና ይጠይቃል። ሲል በማሕበሩ ሊቀመንበር ተፈርሞ ለንግድ ባንኩ ፕሬዝዳንት ቢሰጥም ተቀባይነት አላገኘም የሚሉት የውስጥ አዋቂ ምንጮች ማስፈራራት እና ዛቻ የሚደርስበት ማሕበሩ የሰራተኛውን ጥቅም ለማስከበር እየታገለ ነው ይላሉ።






