የቲሊሊ ፋኖዎቻችን ማስደመሙን ቀጥለውበታል። መብረቆቹ የቲሊሊ ፋኖዎች የተካኑበትን ኦፕሬሽን ነድፎ የመፈፀም አቅማቸውን ዳግም ለማሳየት አቅደው ተቀምጠዋል። ቀኑም ደረሰና በዛሬው ዕለት ማለትም አርብ 26/4/2016 ዓ.ም መብረቆቹ ተወርውረው የጠላት ኃይል ሰፍሮ ወደሚገኝበት አዲስ አለም ትምህርት ቤት በድንገት ከተፍ አሉ።
ከዛም በርካታ አራዊት ሰራዊት በቅፅበት ወደ አስክሬንነት ቀየሩት። ኦፕሬሽኑን ፈፅመው ሲወጡም፦
1ኛ ሁለት ብሬን
2ኛ አንድ ስናይፐር
3ኛ ብዙ ቁጥር ያለዉ ክላሽ በምርኮ ይዘው፣ በርካታ የጠላትን አስክሬን ትተው ነበር።
በጎጃም ደጀን ወረዳ ሸብሸጎ የገጠር ቀበሌ የገባው የጨቅላው አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት በአካባቢው ያለውን ጥብቅ ደን በእሳት እያቃጠለው እንደሚገኝ ታውቋል፤ ቃጠሎው ጠዋት 1:50 እንደጀመረና አሁንም ደኑ እየነደደ ይገኛል ተብሏል። ይህን ቃጠሎ ለማጥፋት በጡሩምባ ህዝቡ ቢወጣም አራዊት ሰራዊቱ ድሽቃ ጠምዶ ህዝቡን እንደመለሰም ታውቋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የጨቅላው ሰውበላ የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ዛሬ በቲሊሊ አዲስ አለም በደረሰባቸው ከባድ ሽንፈትና ውድመትን ተከትሎ በከተማዋ ያሉ 7 ንፁሐን ወጣቶችን መረሸናቸው ተረጋግጧል።
