January 6, 2024 – Konjit Sitotaw 

(ኢትዮ 360- ታህሳስ 27/2016) በጎንደር አይባ ኪዳነ ምህረት ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርን ሊወጋ የገባው ገዳይ ቡድን ሙትና ቁስለኛውን ለመቁጠር እስኪያስቸግር በፋኖ ጥይት መርገፉን የፋኖ ሃይል አመራሮቹ ለኢትዮ 360 አስታወቁ።

ከዚህ ጥይት አምልጦ ወደ ከተማው ማረሚያ ቤት ሲፈረጥጥ የነበረው የሰው በላ ሃይልም መሃል ላይ ተቆርጦ እንዲቀር መደረጉንም ገልጸዋል።

የደረሰበት ድንገተኛ ሽንፈት ያስደነገጠው የገዳዩ ቡድን ስብስብስ ብረት ለበስ ታንክ እና ሞርተር ከማረሚያ ቤቱ አካባቢ ወደ አይባ ኪዳነምህረት እየተኮሰ የአርሶ አደሩን ቤት እያወደመ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የፋኖ ሃይል ደግሞ ከቀበሌ 18 በታች በኩል በቤዛዊት ማርያም አካባቢ ቆርጦ ገብቶ የጠላትን ኃይል በግቢያ መውጫ አሳጥቶታል ብለዋል።