
ከ 5 ሰአት በፊት
ጭንብል ያጠለቁ ታጣቂዎች በቀጥታ ሥርጭት ስቱዲዮ ሰብረው በመግባት ጋዜጠኞችን አገቱ።
በቀጥታ ሥርጭት ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችና ሌሎች የቴክኒክ ባለሙያዎች በታጣቂዎቹ የታገቱት ለአጭር ሰዓት ነው።
ፖሊስ የታገቱትን የስቱዲዮ ባለሙያዎችንና ጋዜጠኞችን በሙሉ አስፈትቻለሁ፤ 13 ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ብሏል።
በኢኳዶር አንድ ሞገደኛ የአደገኛ እጽ ሰንሰለት መሪ ከከርቸሌ ካመለጠ በኋላ በአገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል።
የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ኖቦዋ አስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል።
አዋጁ የሚቆየው ለ60 ቀናት ነው።
እስከ አሁን በአገሪቱ እስር ቤቶች በተነሳ ነውጥ 10 ሰዎች ተገድለዋል።
- ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የገቡት ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው ለምንድን ነው?9 ጥር 2024
- አንዱ የሰውነት አካል ከሌላው አንጻር በፍጥነት እያረጀ መሆኑን ማወቅ ይቻላል?ከ 6 ሰአት በፊት
- የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የጨዋታ ፕሮግራም9 ጥር 2024
የኢኳዶር ጎረቤት የሆነቸው ፔሩ የፖሊስ ኃይል ወደ ድንበር አስጠግታለች። ይህም የሆነው ነውጡ ወደ አገሯ እንዳይሸጋገር በመስጋት ነው።
አሜሪካ በኢኳዶር የተነሳውን አመጽ ያወገዘች ሲሆን ለኢኳዶር ፕሬዝዳንት ማንኛውም እርዳታ እንደምታደርግ ይፋ አድርጋለች።
ኢኳዶር የዓለማችን ከፍተኛ ሙዝ ላኪ አገር ናት። ከሙዝ ሌላ ነዳጅ፣ ቡና፣ ኮኮዋ፣ ሽሪምፕ እና የዓሣ ምርቶችን ወደ ውጭ ትልካለች።
በኢኳዶር የአደገኛ እጽ ነጋዴዎችና አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ አለመረጋጋትን በተደጋጋሚ ይፈጥራሉ። ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሚላኩ የኮኬይን እጽ ለመቆጣጠር በሚደረገው ሽኩቻ አገሪቱ ሰላም ስታጣ ይህ የመጀመርያው አይደለም።
ትናንት ማክሰኞ በቴሌቪዥን ስቱዲዮ በነበረው እገታና ጥቃት አንድ ጭምብል የለበሰ ታጣቂ ሽጉጥ በጋዜጠኛ ላይ ደግኖ ይታይ ነበር።

ሌላ ታጣቂ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ጣልቃ እንዳይገቡ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ ቅረጹኝ እያለ ሲጠይቅ ነበር።
ሌላ ሴት ደግሞ “እባካችሁ አትተኩሱ’ እያለች ስትማጸን በቀጥታ ተላልፏል።
አንድ ሌላ የቴሌቪዥን ሠራተኛ ለኤኤፍፒ በዋትስአፕ ባሾለከው መረጃ “ሊገደሉን መጥተዋል። እዚህ ስቱዲዮ ነው ያሉት። ፈጣሪ ሆይ አድነን። ወንጀለⶉቹ በቀጥታ ሥርጭት ላይ ናቸው” ሲል መልእክት ልኮ ነበር።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአገሪቱ እስር ቤቶች ውስጥ የአደገኛ እጽ አዘዋዋሪ አደገኛ ቦዘኔዎች አስነሱት በተባለ ነውጥ በርካቶች ተገድለዋል።
ነውጦቹ ብዙውን ጊዜ በአደገኛ እጽ ቡድኖች መካከል የሚነሱ ናቸው።
ኮኔሮስ የሚባለውና የኢኳዶር አደገኛ የእጽ አዘዋዋሪ ቡድን እንደሆነ የሚነገርለት ኃይል በአገሪቱ ለሚነሱ አመጾች ዋንኛው ተጠያቂ ይደረጋል።
ፊቶ በሚል ስም የሚታወቀው የቡድኑ አደገኛና ሞገደኛ መሪ ጥብቅ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ማምለጡን ተከትሎ ሁለት የከርቸሌው ጠባቂዎች ምናልባት እንዲያመልጥ ሳይረዱት አይቀሩም በሚል በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የፊቶ ማምለጥ ለወጣቱና አዲሱ ፕሬዝዳንት መጥፎ ዜና ሆኗል።
ፕሬዝዳንቱ በኢኳዶር የአደገኛ እጽ ሰንሰለትን እበጣጥሳለሁ ብለው ቃል ገብተው ነበር በቅርብ ጊዜ ወደ ሥልጣን የመጡት።
በዚህ የፕሬዝዳንቱ ምርጫ እጩ የነበሩትና ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት የተሰጣቸው ፈርናንዶ ቪላቪሴንሲዮ በታጣቂ መገደላቸው አይዘነጋም።
ፈርናንዶ ቪላቪሴንሲዮ ከዚህ ፊቶ ከሚባለው ሞገደኛ አደገኛ ቦዘኔ የሞት ዛቻ በደረሳቸው በማግስቱ ነበር የተገደሉት።
ኢኳዶር በደቡብ አሜሪካ የምትገኝና ፔሩና ኮሎምቢያን የምትጎራበት አገር ስትሆን ሕዝቧ 17 ሚሊዮን ይጠጋል።