January 10, 2024 – Konjit Sitotaw

ከታህሳስ 27 ቀን 2016 እስከ ታህሳስ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በፋኖና በአገዛዙ ወታደር መካከል ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዷል። በዚህም በጎንደርና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ ድሎችን የተቀዳጄ ሲሆን አገዛዙ ቀኑም እንደ ሌሊቱ ጨልሞበት ድል እርቆት ሸንፈቱን ተከናንቧል።
በዚህ የተበሳጨውና ከሽንፈት በኋላ ንጹሃንን የሚያጠቃውና የሚጨፈጭፈው ዐብይ አህመድ በጎንደር ከ60 በላይ ንጹሃንን ገድሏል፤ ከ100 በላይ ንጹሃንን ማቁሰሉን የኢትዮ 251 ሚዲያ ዘጋቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል።
ከታች በምስሉ እንደሚታየው የንጹሃንን ቤት በከባድ መሳሪያ አውድሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘመናዊያኑ የትሮይ ፈረሰኞች የራሳቸውን ወገን ለጠላት አሳልፈው በመስጠት ነው።
የእነዚህ ነውረኞች አምሳያዎች ደግሞ እንደ ተመስገን ጥሩህ፣ ሙሉሸን ሰጥዬ እና መንገሻ ፈንታው ይገኙበታል።
ሶስቱ የዐቢይ አህመድ የትሮይ ፈረሰኞች ፤ የአገዛዙ ነውረኛና ወራሪ ሠራዊት ጎንደር ከተማ ላይ የፈጸመውን ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ለመደበቅ እየሠሩ ይገኛሉ።
የብርሀኑ ጁላ ጦር ጎንደር ላይ ከ60 በላይ ንጹሃንን ጨፍጭፏል፤ ከመቶ በላይ አቁስሏል፤ የቀበሌ 18ን ቀበሌ ጽ/ቤትን በከባድ መሣራያ (Artillery)አፍርሷል።
ይህን ነውር ለመደበቅና ፋኖ ላይ ለማላከክ ሀሰተኛ ዘጋቢ ፊልም ሊያዘጋጁ መሆኑን የኢትዮ 251 ምንጮች ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።
